የፍትህ ሚኒስቴር የ2010 ዓ.ም የዓመቱ የእቅድ አፈጻፀም ማጠቃለያ ሪፖርት

2010 ዓ.ም

Annual Fiscal Plans & Reports

ሀገራችን ኢትዮጲያ የጀመረችውን የህዳሴ ጉዞ ስኬታማና ውጤታማ እንዲሆን ከማድረግ አንፃር ተቋማችን ተልዕኮው ሠፊ ነው፡፡ በመሆኑም ይህንኑ ተልእኮ መወጣት ያችል ዘንድ ከመንግስት በአዋጅ የተሠጠውን ኃላፊነትና ሥልጣን በተለይም ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን ከማክበርና ከማስከበር፣ የህግ የበላይነትን ከማረጋገጥና የወንጀል ህጉን ከማስከበርና የፌዴራል መንግስቱንና የህዝብን ፍትሐብሔራዊ መብትና ጥቅም ከማስጠበቅ አኳያ ሀገራዊ ተልዕኮውን ከማሳካት አንፃር በእቅድ ዘመኑ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ ቆይቷል፣ እያደረገም ይገኛል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን የተፈጠረውን አንጻራዊ ሠላም በዘላቂነት ለማስቀጠል በተለይም የወንጀል ፍትህ አስተዳደሩን ውጤታማነት ከማሳደግና የህዝብና የመንግስት ጥቅም በማስጠበቅ ረገድም የፍትሐብሔር ፍትህ አስተዳደር  ውጤታማነት ለማሻሻል ጥረቶች ከመደረጋቸው ጋር ተያይዞ ህጎችን ከማርቀቅና ችግር ፈቺ ጥናቶችንና የንቃተ ህግ ትምህርትና ሥልጠናዎችን በመስጠት የህብረተሰቡን ንቃተ ህግ ለማሳደግ፣ የገንዘብ አቅም ለሌላቸው ዜጎች የነፃ
የጥብቅና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል በቀጣይም ተጠናክሮ የሚተገር ይሆናል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የሰብዓዊ መብት ድርጊት መርሀ ግብርን በማስፈጻምና ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ከመከላከልና የባለ ብዙ ዘርፍ ጉዳዮችን አካቶ ከመተግበር አኳያ የፍትህ አፈፃፀሙን በህዝብ ግንኙነት በማጀብ ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆኑ ሠፊ
ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ በቀጣይም በተለይ ከሰብኣዊ መብት አያያዝ አኳያ ልዩ ትኩረት የሚሠጠው ጉዳይ ይሆናል፡፡ በበጀት ዓመቱ እንደተቋም ልናከናውናቸው ያቀድናቸውን ግቦች ከማከናወን አንጻር በየደረጃው ውጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን ውስነነቶችም እንደነበሩ ማየት ተችሏል፡፡ በመሆኑም የተመዘገቡ ውጤቶችን በማጠናከር እንዲሁም ክፍተቶችን
ለይቶ በማካተት የተቋሙ የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በቁልፍና ዓበይት ተግባራትና በተመረጡ ተቋማዊ ስትራቴጂካዊ መስኮች በመለየት ለማቅረብ ተሞክሯል፡፡ ሪፖርቱ በዋናነት በአራት ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን በክፍል አንድ – በዝግጅት
ምዕራፍ -የተከናወኑ ተግባራት በክፍል ሁለት – በግትበራ ምዕራፍ የቁልፍና የዓበይት ተግባራት ጥቅል አፈፃፀም በክፍል ሦስት የፕሮጀክቶች አተገባበር እንዲሁም በክፍል አራት የታዩ አፈጻፀም ክፍተቶችና የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች የሪፖርቱ አካል እንዲሆኑ ተደርጎ ከተቀመጡ የተቋሙ ዋና ግቦችና ከሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ግቦች ጋር አፈፃፀሙን በማነፃፀር እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ተጨማሪ ዕቅዶችና ሪፖርቶች

ጥቅምት፥ 2018 ዓ.ም

Annual Fiscal Plans & Reports
መጋቢት 2015

Annual Fiscal Plans & Reports