•
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. መንግስት ፈጣን፣ ፍትሐዊ፣ ቀጣይነትና ዘላቂነት ያለውና የሕዝብ ታጠቀሚነት የተረጋገጠበት ልማትን ለማምጣት እና ዲሞክራሲንና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ፖሊሲና ስትራቴጂና የሁለተኛውን ሀገራዊ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በማዘጋጀት የተጀመረውን ሀገራዊ የህዳሴ ጉዞ ለማሳለጥ በለውጥ ጉዞ ላይ ትገኛለች፡፡ ይህንኑ ራዕይ ለማሳካት የፍትህ ሚኒስቴር በህግ በተሠጠው ሥልጣንና ተግባር ለመወጣት ከሀገራዊ ሁለተኛ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መነሻ በማድረግ ከባለፉት ዓመታት በተቋሙ ከተመዘገቡ ለውጦች አንፃር የ5 ዓመት ሰትራቴጂያዊ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በማቀድ ከዚሁ እቅድ የተመነዘረ የ2008 በጀት ዓመት መሪ እቅድ በማዘጋጀት ለህግ የበላይነት መረጋገጥና ለዜጎች ፍትሐዊ ተጠቃሚነት መጎልበት መልካም አስተዳደርን ለማስፈን፣ ፍትህና ዲሞክራሲን ለማረጋገጥና ልማቱ ቀጣይነት ሰፊ ርብርብ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ወጥነት ያለው ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ተደራሽነቱን የሚያረጋግጥ የፍትህ አገልግሎት ለመስጠት ያመች ዘንድ የህዝብና የመንግስት ጥቅም በተሟላ ሁኔታ የሚያስጠብቅ የህ አስከባሪ ተቋም ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ ቀደም ሲል በተለያዩ ተቋማት ማለትም በፍትህ ሚኒስቴር፣ በፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ በገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣንና በንግድ ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ተበታትነው ይሠሩ የነበሩ የዓቃቤ ህግ ሥራዎችን በማጠቃለል በአዋጅ ቁጥር 943/2008 የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ተቋቁሟል፡፡ በዚሁ መሠረት በ2008 በጀት ዓመት በአዲስ መልኩ ከተቋቋመ በኃላ እንደ ፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የተከናወኑ ተግባራት ዓመታዊ አፈጻጸም በተመረጡ ተቋማዊ የትኩረት መስኮች በመለየት የቁልፍና ዓበይት ተግባራት ክንውንን ባካተተ መልኩ የበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ ሪፖርት ተዘጋጅቷል፡፡ ይህ ሪፖርት በዋናነት በአራት ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን በክፍል አንድ- የመ/ቤቱ ራዕይ ተልኮና እሴቶች በክፍል ሁለትየቁልፍ ተግባራት አፈፃፀም በክፍል ሦስት- ስትራቴጂክ የትኩረት መስኮች አፈፃፀም (ዓበይት ተግባራት) በክፍል አራትየታዩ ጠንካራ አፈጻፀሞችና ክፍተቶች፣ የክትትልና ድጋፍ ሥርዓት አተገባበርን በማካተት ተዘጋጅቶ የቀረበ የዓመቱ ማጠቃለያ እቅድ አፈጻፀም ሪፖርት ነው፡፡
•
•