•
ኢትዮጵያ ሀገራችን ከድህነት ተላቃ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ እንድትሰለፍ ለማድረግ የሚያስችሉ ፓሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ተቀይሰው መተግበር ከጀመሩ ከአስር አመታት በላይ አስቆጥሯል፡፡ በነዚህ ሀገራዊ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በመታገዝ የልማት፣ የሰላም እንዲሁም የተገነባውንና እየተገነባ ያለውን የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ውጤቶችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሽጋገር የ5 ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተነድፎ
በትግባራው ማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ ይገኛል፡፡ የፍትህ ሚኒስቴር ለነዚህ ሀገራዊ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ስኬት የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጠትና
የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሕገ መንግስቱንና ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለማክበርና ለማስከበር፣ የሚያስችል የ5 ዓመት ስትራቴጂያዊና ዓመታዊ ዕቅድ ነድፎ ላለፉት አራት ዓመታት ሲተገባር ቆይቷል፡፡ በተለይም መንግስትን በህግ ጉዳዮች በማማከር የህግ ጥናት በማድረግ በማርቀቅና በማስረጽ እንዲሁም ወንጀሎች የሚቀንሱበትን
ስልት በመንደፍ ብሎም በመከላከልና የወንጀል ስጋቶችን በመቀነስ የተረጋጋ ሥርዓት በመፍጠር የአገሪቱን ልማት ለማፋጠንና ቀጣይነት ለማረጋገጥ፣ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን በሚደረገው ሁለንተናዊ ርብርብ የበኩሉን ድርሻ ሲያበረክት ቆይቷል፣ እያበረከተም ይገኛል፡፡ በዚሁ መሠረት በ2006 በጀት ዓመት በተደረገው የእቅድ አፈጻፀም ግምገማ የአመለካከት፣የክህሎት የአሠራርና
የአደረጃጀት ክፍተቶችን በመለየትና የአፈፃፀም አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የመነሻ ሁኔታዎችን በመውሰድ በዋናነት በቁልፍና ዓበይት ተግባራት ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች መከናወናቸውን በተግባር አፈጻፀማችንን ግምገማ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
በመሆኑም ባሣለፍነው በጀት ዓመት የታዩትን ክፍተቶች በመለየት የ2007 በጀት ዓመት እቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተገብቷል፡፡ በዚሁ መሠረት ሪፖርቱ የበጀት ዓመቱን 8 ወር የሚሸፍን ሆኖ በሦስት ክፍል የተከፈለ ሲሆን በክፍል አንድ የዝግጅት ምዕራፍ የዕቅዱ አፈፃፀም የሁኔታ ግምገማ፣ በክፍል ሁለት የቁልፍ ተግባራት አፈጻፀም በክፍል ሦስት የዓበይት ተግባራት አፈፃፀምና በአፈጻፀም ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሔ ርምጃዎችን እንዲሁም የቀጣይ 4 ወራት የትኩረት አቅጣጫዎችን በማካተት ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
•
•