የመልካም አስተዳደር  ሪፎርም ክላስተር  የመጀመሪያው አምስት ዓመታት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ሪፖርት

መስከረም 2006

Long-Term Fiscal Plans

በአገራችን እየተካሄደ ያለውን የህዳሴ ጉዞ ዳር ለማድረስ ሰፊና ሁለንተናዊ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል፡፡ በአለፉት ዓመታት በተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራት የአገራችን ኢኮኖሚ ባለሁለት አሀዝ ተከታታይ ዕድገት ማስመዝገብ ችሏል፡፡ የኢኮኖሚ ዕድገቱ ፈጣንና ለተከታታይ አስርት ዓመታት የዘለቀ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ፍትሃዊና ሕዝቦችን በየደረጃው አሳታፊና
ተጠቃሚ ያደረገ ነው፡፡ የህዳሴያችን ጉዞ በኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ፍትሀዊ ተጠቃሚነት መስክ ብቻ ሳይሆን በሰላም፣ በዴሞክራሲና በመልካም አስተዳደር መስክም ውጤቶች የተመዘገቡበት ነው፡፡ ዴሞክራሲያችን ሕዝቦቻችንን በአሳተፈና ባለቤት በሚያደርግ አግባብ
ስር እየሰደደ የመጣበት በዚህም የሕዝቦቻችንን ንቁ ተሳታፊነት ባረጋገጠ አግባብ እየዳበረ ያለበት፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ደረጃ በደረጃ እየተቀረፉ የመጡበትን ነባራዊ ሁኔታ መመልከት ይቻላል፡፡ በዚህም ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ተሳትፏችን እያደገና የሀገራችንም መጥፎ ገጽታ እየተቀየረ መጥቷል፡፡
የፍትህ ዘርፉ ልማትን በማፋጠን፣ ዲሞክራሲ፣ መልካም አስተዳደር እና የሕግ የበላይነትን የማስፈን እንዲሁም የዜጐችን መብቶችና ነፃነት የማስከበርና ተጠቃሚነታቸውንም የማረጋገጥ አላማ ያላቸው ተቋማትን ያቀፈ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ክላስተሩ ሕገ መንግስቱን፣ ሕጎችንና በኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት እንዲሁም በመልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲያዊ
ሥርዓት ግንባታ የተቀመጡትን የመንግስት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በብቃት ለማስፈጸም የሚጠበቅበትን ሀላፊነት ለይቶ ለተግባራዊነቱ በትጋት መንቀሳቀስ ይኖርበታል፡፡
በመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን በፍትህ ዘርፉ በታቀፉ ተቋማት የለውጥ ስራዎች በመተግበር፣ የሀገሪቱ ሰላምና ደህንነት እንዲሰፍንና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ፣ ሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት ለልማትና ለዕድገታችን
እንቅፋት እንዳይሆን፣ የፌደራል ስርዓቱ እንዲጠናከርና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን በርካታ ውጤታማ ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል፡፡ በአጠቃላይ በአምስት አመቱ ውስጥ ለዘርፉ የተቀመጡ የአምስት ዓመት ዕቅድ ዋና ዋና አቅጣጫዎችን መሠረት በማድረግ
በተቀናጀ መልኩ ዕቅዱን ለማሳካት የተደረጉት ጥረትና የተወጡት ኃላፊነት በአፈፃፀም ሂደት ውስጥ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎችን በማካተት እና በማነፃፀር የተመዘገቡ መሻሻሎችን በሚያሳይ መልኩ የሰው ኃይል ብቃት
በማጎልበት፤ የፍትህ ዘርፉን ውጤታማነት፣ቅልጥፍናን ከማሳደግ፣ የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ፣ የፍትህ ዘርፉን ግልፅነትና ተጠያቂነት ማረጋገጥ ፣የዳኝነት ነፃነት፣ ግልፅነትና ተጠያቂነትን ማሻሻል፣ የአገልግሎት ተደራሽነትን፣ ዉጤታማነትንና
ተገማችነትን ማጎልበት፣ ታራሚዎችን ማነፅ፣ ጠንካራና የተረጋጋ ፌዴራላዊ ሥርዓት መመስረት፣ የሕዝብና የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ማሳደግ፣ የዘርፉን የለዉጥ ኮሙኒኬሽን ማሻሻል፣ ለዉጡን በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በመደገፍ የመጠቀም አቅምን ማሳደግ እና ባለብዙ ዘርፍ ጉዳዮች በሚሉ ማዕቀፎች ስር የተዘጋጀ አፈፃፀም ተካቶ እንደሚከተለዉ
በዝርዝር ቀርቧል፡፡

ተጨማሪ ዕቅዶችና ሪፖርቶች

ጥቅምት፥ 2018 ዓ.ም

Annual Fiscal Plans & Reports
መጋቢት 2015

Annual Fiscal Plans & Reports