የሗላሸት አግዝ

ዋና ዳይሬክተር
ነሐሴ 1፣ 2014 ዓ.ም. – አሁን

የሗላሸት አግዝ ከነሃሴ 1/2014 ዓ.ም ጀምሮ የሃብት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር በመሆን በመምራት ይገኛል፡፡ በእርሱ አመራር የፋይናንስ፣ የግዠ፣ የመሰረታዊ አገልግሎቶች፣ የሰው ሃብት አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ ስራዎችን በመምራት ለተቋሙ አስፈላጊ የሆኑ የግብዓት ና የሰው ሃይል አቅርቦቶችን በማሻሻል፣ በሲስተም አሰራሮችን በመተግበርና አገልግሎቱን ሊያዘምኑ የሚችሉ አሰራሮችን በመዘርጋት ለተቋሙ ራዕይ መሳካት የዘርፉን ድርሻ እያበረከተ ይገኛል፡፡

የሗላሸት አግዝ ተቋሙን አስተዳደር ስራዎችን በተለይ የክፍያ፣ የግዥ፣ የንብረት፣ የጠቅላላ አገልግሎት፣ የትራንስፖርት ስምሪት፣ የአስተዳደር የሰው ሃይል ስምሪት ስራዎችን በማስተባበር፣ የተለያዩ የመያድ ድርጅቶች (የአውሮፓ ህብረት፣ ዩኒሴፍ፣ ጂአይዜድ የመሳሰሉትን) በጀት ድጋፍን በማስተዳደር ፈጣን አገልግሎት በመስጠትና ምላሽ ሰጪ በመሆን፣ ችግሮችን ለይቶ በመፍታት፣ ውሳኔ በመስጠት ለተቋሙ አጋዥ የሆኑ ደጋፊ ስራዎችን በባለቤትና በቁርጠኝነት ይሰራል፡፡

በተለይ በተለያዩ የሙያና የትምህርት መስኮች የስፔሻላዝድ ኮርሶችን በመማር ራስን ክህሎትና እውቀትን የመሳደግ ስራ ከመስራቱም በተጨማሪ አሁን ካለበት የአመራር ኃላፊነት አስቀድሞ የአስተዳደር ዘርፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የግዥ ዳይሬክተር በመሆን ሲያገለግል ቆይቷል፡፡

የሗላሸት በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ ለ16 ዓመታት በማገልገል በተገኘው ልምድ በተሰማራበት ተቋማዊ የአስተዳደር ስራዎችን የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል ፣ ከተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት፣ ተገልጋይ ተኮር በመሆን፣ ውሳኔ ሰጪ በመሆን ኃላፊነቱን መወጣት ዝግጁና ቁርጠኛ ነው፡፡

የትምህርት ዳራ

  • የመጀመሪያ ድግሪ ከሃዋሳ ዩንቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ
  • የሁለተኛ ድግሪ በትራንስፖርት፣ በፕላኒግና ማኔጅመንት