የሃብት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር በፍትሕ ሚኒስቴር ምንስቴር ስር የተደራጀ የሰው ሃብት ብቃትና አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ፣ የፋይናንስ ስራ አስፈፃሚ፣ የግዥ ስራ አስፈፃሚ፣ የመሠረታዊ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ እና የህንፃና ፋሲሊቲ አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ በስሩ ይዞ የተዋቀረ የአስተዳደር ስራዎችን የሚመሩ ስራ አስፈፃሚዎችን የሚመራ ነው፡፡ የሃብት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ተቋሙ ለተለማቸው ግቦች አስፈላጊ የሆኑ የክፍያና የበጀት አስተዳደር፣ የግብዓት ዓቅርቦት፣ የሰው ሃብት ልማትና አስተዳደር፣ የንብረት አያያዝና አስተዳደር፣ የተሽከርካሪ ስምሪትና አስተዳደር፣ የህንፃ አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ስራዎችን ከፋይናንስ፣ ከግዥና ንብረት፣ ከሲቪል ሰርቪስ አዋጅና መመሪያዎች አንፃር ተፈፃሚ የሚያደርግ፤ ከተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚገኙ የፋይናንስና ዓይነት ድጋፎችን የማስተዳደር፤ የኦዲት፣ የሪፖርት ክትትልና ድጋፍ ስራዎችን ማከናወን ከተሰጡት ዋና ዋና ተግባሮች መካከል ናቸው፡፡
