ትዕግስት መሐቤ ከየካቲት 2020ዓ.ም ጀምሮ የወንጀል ሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ ማስተግበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤትን ስትመራ ቆይታለች። ከ1960 ጀምሮ ሳይለወጥ የቆየውን የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕጉን ለማሻሻል ከፍተኛ ጥረት አድርጋለች። አዲሱን የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ የማርቀቅ ኃላፊነት ከተሰጣቸው ባለሙያዎች ውስጥ ብቸኛዋ ሴት ናት ።

ትዕግስት አሁን ካለችበት የስራ ድርሻ አስቀድሞ በሁሉም የፌደራል ፍርድ ቤቶች የታክስ እና የጉምሩክ ጉዳዮች አቃቤ ህግ በመሆን ፣ አዳዲስ ሕጎችን በማርቀቅ እንዲሁም ነባር የሕግ ማዕቀፎች ከአለም አቀፍ አሰራሮች የተናበቡ መሆኑን በማረጋገጥ እና ልዩ ትኩረት በመስጠት የተናበቡ እንዲሆኑ አስችላለች።

ትዕግስት ከ15 ዓመታት በላይ በሕግ ዘርፍ ልምድ ያላት ሲሆን በኢትዮጵያ የወንጀል ፍትህ ስርዓት ውስጥ የሚስተዋሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እና ክፍተቶችን ለመፍታት ያተኮሩ ሀገራዊ ፕሮግራሞችን በመንደፍ፣ በመተግበር እና በመምራት ላይ ትገኛለች።

 

የትምህርት ዳራ

  • ሀሮማያ ዩኒቨርስቲ፣ የሕግ ዲግሪ
  • ባርሴሎና ዮኒቨርሲቲ በሕግ ሁለተኛ ዲግሪ