በሀገራችን የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት ዓዋጅ ጸድቆ በቅርቡ ሥራ ላይ እንደዋለ ይታወቃል። ይህ አዋጅ የአስተዳደር ተቋማት በሕግ በተሰጣቸው መመሪያ የማውጣት ስልጣንና ባላቸው ከፊል የዳኝነት ስልጣን መሰረት በዕለት ተዕለት ተግባራቸው ውሳኔ በሚያስተላልፉበት ጊዜ የዘፈቀደ አሰራር እንዳይኖር እና የተገልጋዮች መብት ያለአግባብ እንዳይጣስ ለመከላከል ያለመ ነው። ይህ የክትትል ሪፖርት በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ አፈጻጸምን የሚዳስስ ነው።
ለዚህ ጥናት የመረጃ አሰባሰብ ዘዴ የመጀመሪያ የመረጃ ምንጭ የሆኑትን የሕግ ዳሰሳዎች ያካትታል። ይህም ተቋሙ በአዋጅ 1263/2014 እና በሌሎች ሕጎች የተሰጡትን ስልጣንና ተግባራት መፈተሽ ነው። በተጨማሪም ከመመሪያ አወጣጥና አስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ጋር ግንኙነት ያላቸውን የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎችን ቃለ-መጠይቅና ውይይቶች በማድረግ እንዲሁም በምልከታ መረጃዎች ተሰብስበዋል። እንደ ሁለተኛ የመረጃ ምንጭ ደግሞ በተቋሙ የተሰጡ አስተዳደራዊ ውሳኔዎች እንደ ሰነድ ማስረጃ ተጠቅመዋል።
1. ከመመሪያ አወጣጥና ምዝገባ ጋር በተያያዘ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተጠሪ ተቋማትን ጨምሮ 41 መመሪያዎችን በፍትህ ሚኒስቴር ማስመዝገቡ፣ እንዲሁም ከመመሪያ ተደራሽነት አንጻር በከፊልም ቢሆን በድረ-ገጽ ላይ የመጫን ተግባር ማከናወኑ እና ረቂቅ መመሪያዎችን ለአስተያየት ወደ ፍትህ ሚኒስቴር የመላክ አሰራር መጀመሩ አዎንታዊ ነው።
ሆኖም ግን፣ አሉታዊ ጎኖቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-
2. ከአስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥና ቅሬታ አቀራረብ ጋር በተያያዘ የአስተዳደር ውሳኔ ይሰጠኝ አቤቱታ በጽሁፍ እንዲቀርብ የሚያስችሉ ቅጾች መኖራቸው፣ ተገልጋዮች የሚያቀርቡት የሰነድ ማስረጃ የመመልከት አሰራር መኖሩ፣ እንዲሁም የአስተዳደር ውሳኔ በጽሁፍ ለተገልጋዩ የመስጠትና ቅሬታ ተቀብሎ የማስተናገድ አሰራር መኖሩ አዎንታዊ ናቸው።
ይሁን እንጂ፣ የሚከተሉት አሉታዊ ጎኖች ታይተዋል፡-
በዚህ የክትትል ሪፖርት መሰረት፣ የታዩ ክፍተቶችን ለማረም እንዲያስችል የሚከተሉት ምክረ-ሀሳቦች ቀርበዋል፡-