ቀን: ጥር 2016 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን
Ethiopian Revenue and Customs Authority

የፌደራል አስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 አፈፃፀም በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የዳግም ክትትል ሪፖርት

በዚህ ዲግም ክትትል ሪፖርት ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 አፈፃፀም አስመልክቶ በተደረገው ክትትል የተገኙ ክፍተቶች ላይ ማስተካከያ እንዲደርገባቸው የተሰጡ ምክሮች ተግባራዊ መደረጋቸውን ለማረጋገጥ ተሞክሮአለሁ።

ይህንን ክትትል ለማካሄድ የመጀመሪያ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ የመረጃ ምንጮችን ተጠቅመአለሁ። የመጀመሪያ ደረጃ መረጃዎች የጉምሩክ ህጎች እና በደረጃዎች ያሉ የተቋሙ የስራ ክፍል ኃላፊዎች ጋር የተደረገ ቃለ-መጠይቅ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ የመረጃ ምንጮች ደግሞ የተለያዩ የአቤቱታ ማቅረቢያ እና መቀበያ ቅጾች፣ የመለስ መስጫ ቅጾች፣ የውሳኔ ናሙናዎች እንዲሁም በኮሚሽኑ የቀደሙትን የክትትል ሪፖርቶች ተጠቅመአለሁ።

የናሙና አወሳሰድ ዘዴ በተመለከተ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት ዓላማ-መር (purposive sampling technique) ተጠቅመአለሁ። የተሰበሰቡ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ መረጃዎችን በመውሰድ እንዲሁም ቀደም ሲል ያለውን እና አሁን ያለውን የተቋሙን አሰራር በማነጻጸር ግልጽ በሆነ ሁኔታ ለመተንተን ተሞክሮአለሁ።

የዲግም ክትትል ግኝት እንዲያሳየው ከአቤቱታ አቀራረብ ጋር በተያያዘ የኦንላይን ሥርዓቱ በአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ መሠረት ይዞታቸው የተሟሉ አቤቱታዎችን በአማርኛም ሆነ በእንግሊዝኛ ከደጋፊ ማስረጃዎች ጋር በሰነድ መልክ በማያያዝ ማቅረብ በሚያስችለው መልኩ መሻሻለን፣ እንዲሁም የሚሰጡ ውሳኔዎች አዋጁ የውሳኔ ይዘት በሚያስቀመጣቸው መሠረቶች በሙሉ መልኩ ለተጠቃሚው መስጠቱን አስመልክቻለሁ።

በሌላ በኩል በቅ/ጽ/ቤቶች ደረጃ ያሉ የጉምሩክ ጉዳዮች የአቤቱታ አጣሪ የስራ ክፍል የአባል ስብስብ ውስጥ የህግ ባለሙያ እንዲካተትበት ምክር ተሰጥቶ ቢሆንም በአሁኑ ዲግም ክትትል ምክሩ ተፈጻሚ እንዳልሆነ ተረጋግጧል። ስለዚህም በቅ/ጽ/ቤቶች ደረጃ ያሉ የጉምሩክ ጉዳዮች የአቤቱታ አጣሪ የስራ ክፍል የአባል ስብስብ ውስጥ የህግ ባለሙያ እንዲካተት እንዲሁም የኦንላይን ሥርዓቱ ከስራ ቋንቋ አንጻር ዜጎች ግልጽ በሆነ መንገድ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ በሙሉ በሙሉ አማርኛን በፅሁፍ እንዲቀበሉ የማሻሻያ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ምክር ተሰጥቷል።

ሪፖርቱን ያውርዱ

ተጨማሪ ሪፖርቶች