ሕብረተሰቡ አስተማማኝና ዘለቄታዊነት ያለው የውሃ አቅር ቦትና ሳኒቴሽን አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል የውሃ አቅርቦትንና የሳኒቴሽን አገልግሎትን ማጎልበትና ማጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ፣
በምግብ ራስን ለመቻል በሚደረገው የልማት እንቅስቃሴ የመስኖ እርሻ ልማት ከፍተኛ ትኩረት ከሚሰጣቸው ተግባራት አንዱ በመሆኑ ለልማቱ መስፋፋት ምቹ ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
እነዚህንም ዓላማዎች ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊ የሆነውን ገንዘብ ከተለያዩ ምንጮች በማእከል በማሰባሰብ ሁሉም ፍትሐዊና ርትአዊ በሆነ መንገድ ተጠቃሚ የሚሆንበትን አሠራር መቀየስ ተገቢና ለዚሁም የውሃ ልማት ፈንድ ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•