በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥትና በእሥራኤል መንግሥት መካከል ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት እና ዋስትና ለመስጠት ሕዳር 16 ቀን 1996 ዓ.ም ስምምነት በእየሩሣሌም የተፈረመ ስለሆነ፤
ስምምነቱ በሚገባ ሥራ ላይ የሚውለው በተዋዋዮቹ ሀገሮች ሕጎች መሠረት ስምምነቱ መጽደቁን የሚያረጋግጡ ሰነዶች በዲፕሎማቲክ አካላት አማካኝነት ልውውጥ ከተደረገ በኋላ እንደሆነ በስምምነቱ ስለተገለፀ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥር 18 ቀን 1996 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤
በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•