በአገልግሎት ላይ

ከኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ጋር ኢንቨስትመንትን በሁለትዮሽ ለማስፋፋትና ጥበቃ ለመስጠት የተደረገውን ስምምነት ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ

ኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥትና በኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል ኢንቨስትመንትን በሁለትዮሽ ለማስፋፋትና ጥበቃ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ጥቅምት 10 ቀን 1996 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ የተፈረመ በመሆኑ፣

ስምምነቱ ሥራ ላይ የሚውለው በተዋዋይ ሀገሮች ሕጐች መሠረት አስፈላጊ እርምጃዎች ተወስደው በመጨረሻ ላይ አንደኛው ሀገር ለሌላኛው ሀገር ስምምነቱ ሥራ ላይ እንዲውል የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸውን ካስታወቀ በኋላ እንደሆነ በስምምነቱ በመገለፁ፣

ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥቅምት 18 ቀን 1997 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፣

በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት ከዚህ እንደሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 423/1997
ቀን: ህዳር 6፥ 1997 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 399/1996

ሚያዚያ 21፥ 1996 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 389/1996

ጥር 18፥ 1996 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ