በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥትና በኢኳቶሪያል ጊኒ ሪፐብሊክ መን ግሥት መካከል ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋትና ዋስትና ለመስጠት የባለ-ሁለት ወገን ስምምነት ሰኔ 4 ቀን 2001 ዓ.ም በማላቦ የተፈረመ ስለሆነ፤
ስምምነቱ ሥራ ላይ የሚውለው በተዋዋዮቹ አገሮች ሕግ መሠረት መፅደቁን የሚያረጋግጡ ሰነዶች በዲፕሎማቲክ አካላት አማካኝነት ልውውጥ ከተደረገ ከ30 ቀን በኋላ እንደሆነ በስምምነቱ ስለተገለጸ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታህሣሥ 17 ቀን 2002 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፣
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (02) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•