የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ከተለያዩ መንግስታት ጋር ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን የሚፈፅም በመሆኑ፣
በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረጉ ስምምነቶች የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስከበሩ መሆናቸው መረጋገጥ እንዳለበት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀፅ 86(3) የተደነገገ በመሆኑ፤
ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን የመደራደር፣ የመዋዋል፣ የማፅደቅና እና ቀሪ የማድረግ ሥነ ስርዓት ከኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስትና ከሌሎች አግባብ ከሆኑ ሕጐች ጋር ማጣጣም በማስፈለጉ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 51(8) ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን መዋዋልና ማፀደቅ የፌደራል መንግስት ሥልጣንና ተግባር እንደሆነ በመደንገጉ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡