ከዓለም አቀፋዊ የንግድ ልምድ ጋር የሚጣጣም የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎችንና ኢንቨስትመንትን ልማት የሚያበረታታ ፈጣንና ዘመናዊ የጉምሩክ የህግ ማዕቀፍ መኖር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
ሀገሪቱ የምትሳተፍባቸው ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊና ክልላዊ የንግድ ስምምነቶች ዘመናዊ የጉምሩክ ሕጎችንና ሥርዓቶችን ስለሚጠይቁ፤
በህጋዊ ንግድ፣ በህዝብ ደህንነት፣ በመንግስት ገቢ እና በሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማቶች ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እያሳደረ ያለውን የኮንትሮባንድና ሌሎች የንግድ ወንጀሎች እየጨመረ የሚሄድ ክስተት ለመከላከል ከጊዜ ወደ ጊዜ ጠንካራ የህግ ማስከበር ስርዓት አስፈላጊ በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•