የአየር አገልግሎት ስምምነት በኢትዮጵያ ሪፐብሊክ እና በናይጄሪያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ለመጀመር የሚያስችል ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ መንግሥት መካከል እ.ኤ.አ. በጁላይ 5 ቀን 2005 በአቡጃ የተፈረመ በመሆኑ፤
ስምምነቱ በሥራ ላይ የሚውለው በዓለም አቀፍ ስምምነት አፈጻጸምን በተመለከተ ሕገ-መንግሥታዊ ሥነ-ሥርዓቶች መፈጸማቸውን ሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እርስ በርሳቸው ካስታወቁበት ዕለት ጀምሮ እንደሚሆን በስምምነቱ ውስጥ የተመለከተ በመሆኑ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 13 ቀን 1998 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•