ከአሜሪካን መንግሥት ጋር የተደረገ የአየር አገልግሎት ስምምነት ማፅደቂያ አዋጅ

የአየር አገልግሎት ለመጀመር የሚያስችል ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በአሜሪካ መንግሥት መካከል እ.ኤ.አ. ሜይ 17 ቀን 2005 በዋሽንግተን ዲሲ የተፈረመ በመሆኑ፤

ስምምነቱ በሥራ ላይ የሚውለው በዓለም አቀፍ ስምምነት አፈጻጸምን በተመለከተ ሕገ-መንግሥታዊ ሥነ-ሥርዓቶች መፈጸማቸውን ሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እርስ በርሳቸው ካስታወቁበት ዕለት ጀምሮ እንደሚሆን በስምምነቱ ውስጥ የተመለከተ በመሆኑ፤

ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 13 ቀን 1998 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 500/1998
ቀን: ሰኔ 30፥ 1998 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 453/1997

ሰኔ 17፥ 1997 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ