በሀገራችን የጨረራና የኒውክለር ቴክኖሎጂን የመጠቀም ባህል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱና አግባብ ያለውና ውጤታማ የመከላከል ዘዴ በሥራ ላይ እስካልዋለ ድረስ ጨረራ በጤና፣በንብረትና በአካባቢ ላይ ሊያስከትል የሚችለው ተጓዳኝ ጠንቅ እየጨመረ የሚሄድ በመሆኑ፤
ቁጥጥር ሊደረግባቸው የሚገቡ የጨረራ አመንጪዎችና ኒውክለር እና ተያያዥነት ያላቸው ተግባራት ለሕብረተሰቡ ጥቅም አገልግሎት ላይ ሲውሉ በግለሰቦች፣ በሕብረተሰቡ፣ በንብረትና በአካባቢ በአሁኑና በወደፊቱ ትውልድ ጭምር ሊያደርሱ የሚችሉትን ተጓዳኝ የጨረራ ጠንቅ መከላከል በማስፈለጉ፤
ከጨረራ አመንጪና ኒውክለር ቁሶች አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የሚመለከታቸው አካላት ግዴታቸውን በግልጽፅ እንዲያውቁ ለማድረግና ሕግን በመተላለፍ ለሚደርስ የጨረራ ጉዳት ተመጣጣኝ የሆነ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችሉ ሕጎችን በመደንገግ ከዓለም አቀፍ ስርዓቱ ጋር የተጣጣመ የጨረራ መከላከሉን ስራ ማጠናከር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•