እ.ኤ.አ. በ2001 አለም አቀፉ የማሪታይም ድርጅት በመርከብ የፍጆታ ነዳጅ ፍሳሽ ሳቢያ ለሚደርስ የከባቢ ብከላ ጉዳት ስለሚኖር የፍትሐብሔር ሃላፊነት አስመልክቶ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ያወጣ በመሆኑ፤
ይህንኑ ኮንቬንሽን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታህሣሥ 23 ቀን 2001 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•