የጅምላ ጨራሽ መሣሪያዎች ብዜት እና ይህንኑ በገንዘብ መደገፍ ዓለም አቀፍ የደህንነት ስጋት በመሆኑ፤ ሁሉም ሃገራት ይህን ለመከላከል፣ ለመግታት እና ለመቆጣጠር በሚደረጉ ሌላዊ የትብብር ማዕቀፎች በጋራ እና በትብብር እንዲሰሩ በማስገደዱ፤
ኢትዮጵያ የጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎች ብዜትን ከመከላከልና ከመቆጣጠር ጋር ተዛማጅነት ያላቸዉ የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ስምምነቶችን ያፀደቀች በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ውስጥ ሊካሄዱ ወይም ሊያልፉ የሚችሉ የጅምላ ጨራሽ መሣሪያዎች ብዜትን የሚደግፉ ማናቸውንም ተግባራት መከላከልና መቆጣጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤
እያንዳንዱ ሀገር በስምምነቶቹ የተጣሉበትን ኃላፊነቶች ለመወጣት አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን መውሰድ ስለሚጠበቅበት እና ለዚህም አተገባበር ሃገራዊ ህግ ማዉጣት አስፈላጊ በመሆኑ፣
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•