ለሻምቡ-ባኮ የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል መጠኑ 25 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር (ሃያ አምስት ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር) የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በኦፔክ ፈንድ ለዓለም አቀፍ ልማት መካከል እ.ኢ.አ ሜይ 4 ቀን 2015 በዋሽንግተን ዲ.ሲ. የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 30 ቀን 2007 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•
•