ለዲላ-ቡሌ-ሃሮ ዋጩ መንገድ ስራ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል መጠኑ 22 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር (ሃያ ሁለት ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በነዳጅ አምራችና ላኪ አገራት ፈንድ ለዓለም አቀፍ ልማት መካከል እ.ኤ.አ ኤፕሪል 13 ቀን 2019 በዋሽንግተን ዲ.ሲ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•
•