የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት የግሎባል ፈንድ፤ ኤድስን፣ ሳንባ ነቀርሳን እና ወባን ለመዋጋት የልዩ መብቶች እና ከለላዎች ስምምነትን በአንቀጽ 2 (4) እና (8)፣ በአንቀጽ 3 (1) (ረ)፣ በአንቀጽ 3 (3)፣ በአንቀጽ 4 (2) (ለ) ፣ (መ) እና (ረ)፣ እና በአንቀጽ 4 (4) ላይ ተዓቅቦ በማድረግ ሐምሌ 8 ቀን 2003 ዓ.ም የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 26 ቀን 2009 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የመረመረውና በአንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ (2) እስከ (6) ላይ ተጨማሪ ተዓቅቦዎችን በማስቀመጥ ያፀደቀው በመሆኑ፤
የተሰጠው መብትና ከለላ ከምን አኳያ መተርጎም እንዳለበት መግለጫ የቀረበበት ሲሆን ይህም የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በስምምነቱ በግሎባል ፈንድ ለመንግሥት ተወካዮች፣ ለሃላፊዎች እና ለሌሎች ግለሰቦች የተሰጡ ልዩ መብቶች እና ከለላዎች ተፈጻሚ የሚሆኑት በድርጅቱ ውስጥ ያላቸውን ሥራ ለማከናወን በሚያደርጓቸው ተግባራት ላይ ብቻ የሚል መግለጫ የቀረበ በመሆኑ፣
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፦
•
•
•
•
•
•
•