በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ መካከል በገቢ ላይ የሚከፈለውን ግብር በሚመለከት ተደራራቢ ግብርን ለማስቀረት እና በታክስ ላይ የሚፈጸምን ማጭበርበር ለመከላከል የሚያስችል ስምምነት ሚያዚያ 4 ቀን 2007 ዓ.ም በአቡ ዳቢ ከተማ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንን ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዚያ 11 ቀን 2008 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•