በአፍሪካና አውሮእስያ ስደተኛ የውኃ የአእዋፋት ዝርያን ለመጠበቅ እ.ኤ.አ. ጁን 16 ቀን 1999 በኒዘርላንድ አገር በሄግ ከተማ ተፈርሞ ከኖቬምበር 1 ቀን 1999 ጀምሮ በብዙ አገራት በመተግበር ላይ በመሆኑ፤
በዚህም የስምምነት አንቀፅ 13(3) እ.ኤ.አ. ከኖቬምበር 1 1999 በኋላ አባል ለመሆን ፈቃደኛ የሆኑ አገራት ስምምነቱን በማፅደቅ አባል ለመሆን ስለሚችሉ፤
ስምምነቱም በአፍሪካና በአውሮእስያ ስደተኛ የውኃ የአእዋፋት ዝርያን በአባል አገራት ትብብር ለመጠበቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚኖረው በመሆኑ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ግንቦት 27 ቀን 2001 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ- መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀፅ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•
•