ኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ህንድ ሪፐብሊክ መካከል ያለውን የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት በተጨማሪ ለማጠናከር በማስፈለጉ፣
በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን የቪዛ ቅድመ ሁኔታ በማስቀረት ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ያዙ ዜጎች ቪዛ ሳይያስፈልጋቸው በሀገራቱ መግባት እንዲችሉ ለማድረግ፤
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና የህንድ ሪፐብሊክ መንግሥታት መካከል የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ያዙ ሰዎች ቪዛን ለማስቀረት የሚያስችል ስምምነት በካቲት 12 ቀን 2013 ዓ.ም በህንድ ተፈርመ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ3ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ጥቅምት 7 ቀን 2016 ዓ.ም በአካሄደው 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ያጸደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•
•