የጥብቅና አገልግሎት በሕግ ሙያ የሠለጠነና ሰፊ ልምድ ያለው የፍርድ ቤት አሠራርን ጠንቅቆ የሚያውቅ፣የታማኝነት፣ የቅንነትና የእውነተኝነት መንፈስን የተላበሰ ሰው ለሕግ የበላይነትና ለፍትሕ መስፈን ከፍትሕ አካላት ጐን በአጋዥነት የሚሰለፍበት ሙያ በመሆኑ፤
በፌደራል ፍርድ ቤቶች ለመሥራት የሚችሉ ጠበቆችን ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥ ሁኔታ በተሟላ መልኩ በሕግ መደንገግ በማስፈለጉ፤
የጥብቅና ሥራ የሚሠሩ ሰዎችን የሙያ ብቃት ደረጃ ከሚሰጡት አገልግሎት ጋር የተመጣጠነ ለማድረግ በሥራው ለመሠማራት የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን ከፍ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 /1/ መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•