የከፍተኛ ትምህርት የሀገሪቱን የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጎት በብቃት እና በጥራት ለማፍራት የሚያስችለው ሥርዓት መዘርጋትና መመዘኛዎችን ማውጣት አስፈላጊ በመሆኑ፤
በከፍተኛ ትምህርት የሚደረገው ምርምር ችግር ፈቺና የሀገሪቱን ዕምቅ ሀብት ሥራ ላይ እንዲውል የሚያስችል እንዲሆን ተገቢውን የሕግ መደላድል መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያላቸውን ነጻነትና ተጠያቂነት እንዲሁም አስተዳደራቸውን በሕግ መደንገግ በማስፈለጉ፤
የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት በማስፋፋት እና ምርምርን በማስረጽ ረገድ ያላቸውን አስተዋጽኦ ከፍ ለማድረግና አመራራቸውን በሕግ መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•