የአዲስ አበባ ከተማ የመንገድ መብራት አገልግሎት በሽፋን፣ በዓይነትና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም እያደገ መጥቷል፡፡ በመሆኑም ይህንን እያደገ የመጣውን የመንገድ መብረት አገልግሎት ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ በህግና ስርአት መምራት አስፈላጊ ነዉ፡፡ መንግስት ለመሰረተ ልማት ዝርጋታ እና ጥገና ከፍተኛ እያወጣ ይገኛል፡፡ በመንገድ ዳር የሚተከሉ የመብራት መሰረተ-ልማቶች፤ ምሰሶዎች እና በምሰሶዎች የተገጠሙ ስክሪኖች፣ ሲሲቲቪ ካሜራዎች፣ የዋይፋይ መሣሪያዎች እና በአረንጓዴ ቦታዎች የተተከሉ ጌጣጌጥ መብራቶች፣ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች እና መስመሮች ላይ ለሚደርሰው ጉዳት የካሳ ክፍያ ሥርዓት ተዘርግቶ ካልተመራ በሚደርሰዉ ጉዳት ምክንያት የሕብረተሰቡን መብትና ጥቅም እንዲሁም የከተማችንን ገጽታ ሊጎዳ የሚችል በመሆኑና ለመተካትና ለመጠገን ሌላ ተጨማሪ ወጪ የሚጠይቅ ስለሆነ ፣ ጉዳት አድራሽዎች ለምትክ የንብረት ካሳ ክፍያ ማስከፈል በማስፈለጉ የአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን በአዋጅ 84/2016 አንቀፅ 16 ንዑስ አንቀፅ 2(ሠ) በደንብ ቁጥር 166/2016 አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ 3 በተደነገገው መመሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል።
•
•
•
•
•
•