የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ስር በሚገኙ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እየተከናወነ ካለውና እየጨመረ ከመጣው የሥራ ፍሰት አንጻር የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን ተግባራት አቀናጅቶ እንዲመራ እና ክትትልና ድጋፍ እንዲያደርግ እና የቅርብ አመራር በመስጠት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ከስር ከስር እየቀረፉ ውጤታማ ተግባር እንዲያከናውን ለማስቻልም በማሰብ የ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት መቋቋሙ ይታወቃል፡፡
ዳይሬክቶሬቱ ከተገልጋይ አንጻር ከተሰጡት ኃላፊነቶች መካከል አንዱ የሚቀርቡ አቤቱታና እና ቅሬታዎችን ሰንሰለቱን ጠብቀው መቅረባቸውን የማረጋገጥ፣ የማስተናገድ፣ ዉሳኔ የመስጠት እና አፈፃፀሙን የመከታተል ኃላፊነት ይገኝበታል፡፡
በመሆኑም በድሬዳዋ እና ሃዋሳ የሚገኙትን ጨምሮ በአስራ ሁለቱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ላይ ከአገልግሎት አሰጣጥ አንጻር አቤቱታ ወይም ቅሬታ ለማቅረብ ሲፈልጉ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለቡን አለፍ ብሎ ቫርኔሮ አደባባይ አጠገብ የፍትሕ ሚኒስቴር የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚገኝበት ሕንጻ 6ኛ ፎቅ ላይ ወደሚገኘው የ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ቀርበው አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር
ለሕግ ፣ ለፍትሕ ፣ ለርትዕ
በጎግል ማፕ (Google Map) ለመመራት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ