ክፍል ሶስት
1. የንብረት ማሰመለስ ስራ ኃላፊነትን በተመለከተ የተሰጠ ሥልጣን ወይም ኃላፊነት
የንብረት ማስመለስ ስራ የብዙ ተቋማት ቅንጅትን/ትብብርን የሚፈልግ ስራ ሆኖ በተማከለ ሁኔታ በአንድ የሕግ ማስከበር ተቋም/ዐቃቤ ሕግ የሚመራ ስራ ነው፡፡
2. ዐቃቤ ሕግ ራሱ በሚመረምርበት ጉዳይ ላይ ዕግድ ትእዛዝ በራሱ ማውጣቱ ከ check and balance and impartiality አንፃር የማይጋጭ ስለመሆኑ፤
በተመሳሳይ እንደማንኛውም የመንግሥት ስራ ስራው ለብልሹ አሠራር ሊጋለጥ ይችላል፡፡ ነገር ግን ዋናው ቁምነገር ዜጎች ላልተገባ የመብት ጥሰት እንዳይዳረጉ ምን መንገድ አለ የሚለው ጉዳይ ነው፡፡ በመሰረቱ በዚህ አዋጅ ዐቃቤ ሕግ ተቋም (ፍትሕ ሚኒስቴር) አንድም አስተዳዳራዊ በሆነ መልኩ ውርስ ሊፈፅም የሚችልበት ምንም መብት አልሰጠም፡፡ የትኛውም ክርክርም ሆነ ውርስ ትእዛዝ መስጠት የሚችለው ፍርድ ቤት ነው፡፡ በፍርድ ቤት ደግሞ አንዱ ፍርድ ቤት ላይ የተፈፀመን የትኛውንም አይነት ስህተት የማስተካከያ የይግባኝ ስርዐት መኖሩ የታወቀ ነው፡፡ ስለዚህ ከምርመራ የይግባኝ ደረጃውን አልፎ እንስከሚሰጥ የመጨረሻ ውሳኔ ድረስ ሊደርሱ የሚችሉ የስነ ምግባር ግድፈቶችን የሚጣሩበት እና ሊስተካከሉ የሚችልበትን ስርዐት አለው፡፡ ከዚህ ወጪ ፍትሕ ሚኒስቴር ግልፀኝነት የሚፈጥር እና ይህ ስርዐት የሚመራበትን ውስጣዊ የአሠራር ስርዐቶችን በሕግ የሚዘረጋ ይሆናል፡፡ ይህም ጠንካራ የስነ-ምግባር ክትትል እና አቤቱታ መቀበያ ስርዐትንም ያካትታል፡፡
3. ዐቃቤ ሕግ ራሱ በሚመረምርበት ጉዳይ ላይ ዕግድ ትእዛዝ በራሱ ማውጣቱ ከ check and balance and impartiality አንፃር የማይጋጭ ስለመሆኑ፤
ይህ ጉዳይ በዐቃቤ ሕግ ለ72 ሰዓት አስተዳደራዊ ዕግድ የሚሰጥበትን ጉዳይ በተመለከተ ሲሆን ይሀም በተመሳሳይ በዚህ ሕግ አዲስ የመጣ አይደለም፡፡ በሕግ ስርዐታችን ውስጥ ቀድሞም የነበረ ነው፡፡ በፊት ዐቃቤ ሕግ ሃላፊ 48 ሰዐት የማገድ ስልጣኑን በዚህ ሕግ ወደ 72 ሰዐት ከፍ እንዲል አድርጋጓል፡፡ በመሰረቱ ይህ የዕግድ ሁኔታ መርህ ሳይሆን ልዩ ሁኔታ ነው፡፡ ስለዚህ በጠባቡ ነው ስራ ላይ የሚውለው፡፡ አንደኛ ይህን ዕግድ ዐቃቤ ሕግ ሳይሆን የተቋሙ/የዘርፉ የበላይ ሃላፊ ብቻ ነው ሊሰጥ የሚችለው፡፡ ስለዚህ arbitrarly ለሁሉም ባለሙያ የተሰጠ ሥልጣን አለመሆኑን ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ይህ ዕግድ ግዜያዊ እንጂ ገደብ አልባ እና እስከመጨረሻው ጸንቶ የሚቆይ አይደለም፡፡ ዐቃቤ ሕግ ይህን ዕግድ ካሰጠ በኋላ መደበኛ ዕግድ ለፍርድ ቤት አቅረቦ ማስቀየር አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን በአዋጁ የተቀመጡትን የገዜ ገደቦች ወስጥ ዕግዱ ቀሪ የሚሆንበትን አግባብ ተመላክቷል፡፡ ወደ 72 ሰዓት ከፍ ያለው ከዚህ በፊት የነበረው የ48 ሰዐት ዕግድ በተግባር ውጤታማነቱ ላይ ተግዳሮት ስለገጠመው ነው፡፡
4. የመያዝና የዕግድ ትእዛዝ የማያርፍባቸው የንብረት አይነቶች
የእለት መተዳደሪያ ወይም ሙያዊ ሥራ ለመሥራት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች፣ የቤት ውስጥ መገልገያ የሆኑ ዕቃዎች፣ ለእለት ኑሮ የሚሆን እና የስድስት ወር ወይም ፍርድ ቤቱ በልዩ ሁኔታ ለሚወስነው ጊዜ የሚቆይ ስንቅ (ለምግብነት የሚውል) ንብረቶች በመርህ ደረጃ ሊያዙ ወይም ሊታገዱ አይችሉም፡፡ ሆኖም ቁሳቁሶቹ ውድ ከሆኑ ማዕድናት ወይም ከፍተኛ ዋጋ ካለው የእደ ጥበብ ሥራዎች የተሰሩ ከሆነ ወይም ንብረቱ የወንጀል ፍሬ መሆኑ በግልጽ ከታወቀ በምንም ዓይነት ሁኔታ ተጠርጣሪው ወይም ተከሳሹ ከወንጀል ፍሬው የመጠቀም መብት ስለማይኖረው የዕግድ ወይም የመያዝ ትእዛዝ ያርፍበታል፡፡
5. የተወረሰ ንብረት በተመለከተ (እጣ ፈንታ)
በወንጀል የተገኘ ሀብትን ከማስመለስ አንጻር በዓለም-ዓቀፍ ደረጃ የተቀመጡ ስምምነቶች እና የአፈጻጸም ግምገማ ሰነዶች እንዳስቀመጡት አንድ ሀገር በጣም ተጋላጭ የሆነባቸውን የተደራጁና ኢኮኖሚያዊ ወንጀሎች የሚለይበትን ጥናት ማከናወን እንዳለበት እና በዚህ መንገድ የተለዩ ወንጀሎችን በመለየት፣ በመመርመር፣ በመክሰስ፣ ተገቢውንና አስተማሪ ቅጣት በመጣል እንዲሁም የተመዘበረውን ሀብት በማስመለስ ተገቢውን የሕግ ማስከበር ስራ መሥራት እንዳለበት ሲያስገነዝቡ ከዚህ አሠራር ጀርባ ያለው ምክንያት ደግሞ ውሱን የሆነውን ሀብት ለሕግ የበላይነት እና የፍትሕ ስራ ለማዋል ቅድሚያ የሚሰጠው በጣም ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ለሚያደርሰው ወንጀል አይነት ነው በሚል ነው፡፡
ስለሆነም ሁሉንም ወንጀል መርምሮ ክስ ለማቅረብ እና ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድ በቂ ሀብት እንደማይኖር የታወቀ በመሆኑ ምክንያት አንዳንድ ሀገራት በወንጀል የተገኘ ነው በሚል መርምረውና ክስ አቅርበው በፍርድ ቤት እንዲወረስ ውሳኔ የሚያሰጡበትን ንብረት መልሰው ለወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ተግባር ያውላሉ፡፡ በዚህ አግባብ ይህ የንብረት ማስመለስ አዋጅ ተመሳሳይ አቋም በመያዝ ከፋይናንስ ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር የተወሰነውን የተወረሰ ሀብት ለወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ለማዋል የሚቻልበትን ሁኔታ አስቀምጧል፡፡