በፍትሕ ሚኒስቴር ለሚገኙ የስታትስቲክስ እና ዳታ ኢንኮደር ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ተጀመረ

Training Commenced for Statistics and Data Encoder Professionals at the Ministry of Justice

በፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ፣ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት የስታትስቲክስ እና ዳታ ኢንኮደር ባለሙያዎች ”Fundamental of Statics, Data Preparation, and Analysis Using Excel Spread Sheet” በሚል የሥልጠና ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ከግንቦት 19- 21/2017 ዓ.ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጠው ሥልጠና ዛሬ መሰጠት ተጀምሯል፡፡

የሥልጠና መድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የንቃተ ሕግ ፣ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት የምክትል ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ተክለ ልብሰወርቅ እንደተናገሩት ለተቋሙ የስታትስቲክስ እና ዳታ ኢንኮደር ባለሙያዎች ስለጠናውን መስጠት ያስፈለገው በስራ ላይ የሚስተዋሉ የክህሎት ክፍተቶችን ለመሙላት፣ በተቋሙ ውስጥ ወጥ የሆነ የመረጃ አያያዝ ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻል እንዲሁም ደንበኛ ተኮር የሆነ አገልግሎት ለመስጠት አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ነው ብለዋል፡፡ አክለውም ይህን መሰል ሥልጠና መስጠቱ የተደራጁ መረጃዎችን በአግባቡ ለመተንተንና ጥቅም ላይ እንዲውሉ ለማስቻል ከዚያም ባለፈ የባለሙያዎች የስራ ላይ መነቃቃትን ለመፍጠርና የስራ ተነሳሽነታቸውን ለመጨመር የጎላ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡

በሥልጠና መድረኩ በገለጻ መልክ የቀረቡ ርዕሰ ጉዳዮችን መሠረት በማድረግ ሰልጣኞች የተግባር ልምምድ የሚያደርጉ በመሆኑ የተሻለ ግንዛቤን እንደሚፈጥር ተመላክቷል፡፡

Tagged Under: analysis building capacity Capacity Building data data management data processing employee employee training gap government employees Justice Justice Sector Reform management preparation professional development sector skill statistical statistical analysis Training workforce development
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች