መዝገብ አስተዳደር የመረጃ ስርአት(CRIMS) በስፋት ለማስጀመር ያለመ ስልጠና እየተሰጠ ነዉ

Training Aimed at Broadly Launching the Case Record Information Management System (CRIMS) is Being Provided

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የወንጀል መዝገብ አስተዳደር የመረጃ ሥርዓት (CRIMS) በስፋት ለማስጀመር ያለመ ሥልጠና ለፌዴራል መርማሪ ፖሊሶችና ለዐቃቢያነ ሕግ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

በፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኤርሚያስ የማነብርሃን ሥልጠናዉ ሲዘጋጅ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠዉ መሆኑን ጠቁመዉ ሰልጣኞችም በትኩረት ተከታትለዉ ወደ ስራ በሚመለሱበት ወቅት የጨበጡትን እዉቀት በሚገባ ተግባራዊ በማድረግ የፍትሕ ስርአቱን የተሳለጠ ለማድረግ የድርሻቸዉን እንዲወጡ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ተቋሙ በዚህ ዓመት ከያዛቸዉ ግቦች ዉስጥ አንዱ ያደገ የቴክኖሎጅ አጠቃቀምን ማሳደግ ሲሆን የወንጀል መዝገብ አስተዳደር ስርአቱን ከወንጀል ጥቆማ እስከ ማስቀጣት ያለዉን ሂደት በዘመናዊ ቴክኖሎጅ በማስደገፍ የፍትሕ ስርአቱን የተሳለጠ ለማድረግ በማለም ሥልጠናዉ ተዘጋጅቷል፡፡

የመጀመሪያዉ ዙር ሥልጠና ለአምስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በቀጣይም በጥቅሉ አንድ መቶ ለሚደርሱ መርማሪ ፖሊሶችና ዐቃቢያነ ሕግ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

Tagged Under: building capacity Capacity Building case case management system Criminal Justice crims Digitalization Education federal Federal police information information management system Justice Justice System Reform learning Legal technology management Police Prosecutors record reform skill development system Technology technology adoption Training
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች