በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት በ374 መዛግብት ላይ ውሳኔ መስጠቱ ተገለፀ

The Directorate of Public Prosecution for Crimes Against Women and Children Issues Decisions on 374 Cases

በ2015 ዓ.ም የበጀት ዓመት በመጀመሪያው ስድስት ወራት በአዲስ አበባ ከተማ ወደ ሚገኙት የተቀናጀ የፍትሕ እንክብካቤ ማዕከላት በመምጣት አገልግሎቱ ከተሰጣቸው ተገልጋዮች ውስጥ 572 የአስገድዶ መድፈር ወንጀል፣ 40 ደግሞ የግብረ-ሰዶም ጥቃት ወንጀል ተፈፀመብን በማለት የመጡ ሲሆን፣ የወንጀል ድርጊቱም 563 የሚሆኑት ከ18 ዓመት በታች በሆኑ ሴቶችና ሕፃናት እንዲሁም 198 ዕድሜአቸው ከ18 ዓመት በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ የተፈፀመ ሲሆን በብዛት የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመውም በየካ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ እና ቦሌ ክፍለ ከተሞች በመሆኑ በእነዚህ ክፍለ ከተሞች ከሚገኙ የሴቶችና ሕፃናት ጥቃት ተከላካይ ኮሚቴ አደረጃጀቶች ጋር በወንጀል መከላከል ዙሪያ መሥራት ያስፈልጋል ሲሉ ዳይሬክተሯ ገልፀዋል፡፡

ዳይሬክተሯም በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን አስቀድሞ ለመከላከል እንዲቻልም የሴቶችና ሕፃናት መብቶች ለመጠበቅ የተደነገጉ ሕጎችን፣ እየተፈፀሙ ያሉት የወንጀል ድርጊቶችን እና በአዲስ አበባ ከተማ በብዛት ወንጀሉ የተፈፀመባቸው ክፍለ ከተሞችን አስመልክቶ ዳሰሳዊ ጥናት በማዘጋጀት በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ከሴቶችና ሕፃናት ጥቃት ተከላካይ ኮሚቴ አባላት ጋር ውይይት ተደርጓል ብለዋል፡፡

በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች እጅግ ዘግናኝ የሚባሉ የወንጀል ድርጊቶች ከመሆናቸው የተነሳ በተጎጂ፣ በተጎጂ ቤተሰቦች እና በህብረተሰቡ ላይ የሚያደርሱት የስነ-ልቦና ጫና ከፍተኛ ስለሆነ ህብረተሰቡ የሴቶችና ሕፃናትን መብት ለመጠበቅ ሲባል የተደነገጉ ሕጎች እና እየተፈፀሙ ያሉትን የወንጀል ድርጊቶች ግንዛቤ እንዲኖረው በማድረግ በሴቶችና ሕፃናት ላይ ወንጀል እንዳይፈፀም አስቀድሞ መከላከል አበክሮ መሥራት እንደለበ እና ወንጀሉ ተፈፅሞ ሲገኝም በተቻለ ፍጥነትና ጥራት ምርመራው ተከናውኖ የድርጊቱ ፈፃሚዎች በሕግ ፊት ቀርበው ሕጉ የሚፈቅደውን ተገቢ ቅጣት እንዲያገኙና ማድረግ ተገቢ እንደሆነም ዳይሬክተሯ አብራርተዋል፡፡

በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጾታን ወይም ዕድሜን መሠረት በማድረግ ለወንጀል ጥቃት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚፈፀምባቸውን ወንጀሎች የምርመራም ሆነ የክርክር ስራዎችን የመከታተል፣ የማስተባበርና ድጋፍ የመስጠት ተግባራት እንዲያከናውን የተደራጀ ዳይሬክቶሬት በመሆኑ በበጀት ዓመቱ በቀሪ 6 ወራትም በሴቶች እና ሕፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን፣ ወንጀሎችን መከላከል እና የምርመራ ስራን ፈጣንና ውጤታማ እንዲሆን ትኩረቱን አድርጎ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

Tagged Under: ababa • abuse • addis • addis ababa • assault • Case Resolution • child • Child Abuse • Child Protection • Crime Prevention • criminal • Criminal Justice • Dire Dawa • Gender-Based Violence • Investigation • Justice • Legal Decisions • offenders • Prosecution • protection • public • public prosecution • Rape • Rights • sexual • sexual assault • victims • women's • Women's Rights
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች