በልዩ የክረምት ሥልጠና መርሀ-ግብር በወንጀል ምርመራ፣ ክስ ዝግጅት እና ችሎት ክርክር ላይ ያተኮረ ሥልጠና እየተሰጠ መሆኑ ተመላከተ

Special Winter Training Launched on Criminal Investigation, Case Preparation, and Trial Advocacy

በልዩ የክረምት ስልጠና መርሀ-ግብር በወንጀል ምርመራ፣ ክስ ዝግጅት እና ችሎት ክርክር ላይ ያተኮረ ስልጠና Diredawa

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ የፍትሕ ሚኒስቴር ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዐቃቤያነ ሕግ የሚሳተፉበት ልዩ የክረምት ሥልጠና በድሬዳዋ ከተማ በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡

በሥልጠና መድረኩ ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት በፍትሕ ሚኒስቴር የድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ካሳሁን ይህ ሥልጠና በተደጋጋሚ ስንጠይቀው የነበረና የተሻለ ሥራን ለማከናወን የሚያስችል አቅም እና በተለይ በወንጀል ምርመራ፣ የክስ ዝግጅት እና ክርክር ዙሪያ በተግባር የተደገፈ ልምድ የሚገኝበት በመሆኑ ሥልጣኞች ተገቢውን ትኩረት ሰጥተው በንቃት በመሳተፍ አስፈላጊ የሆነ እውቀት መገብየት የሚጠበቅባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ሥልጠናውን በይፋ ያስጀመሩት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸው ወርቁ ሥልጠናው በተግባር የምርመራ መዝገብ እንዴት እንደሚመረመር፣ ማስረጃ እንዴት እንደሚመዘን፣ ክስ እንዴት እንደሚመሠረት እና የችሎት ክርክር እንዴት እንደሚካሄድ በሰፊው ልምድ የሚወሰድበት መሆኑን ጠቅሰው፤ ፍትሕ ሚኒስቴር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራባቸው ከሚገኙ እና በስትራቴጂካዊ የትኩረት መስክ እንደ አንድ አቅጣጫ ከተያዙ ጉዳዮች መካከል በተቋሙ ሙያዊነትን (professionalism) ማስፈን አንዱ መሆኑእና ይህንኑ ለማሳካት በተለያዩ መንገዶች የአቅም ግንባታ ሥራዎች እየተካሄዱ መሆናቸውን፤ ለአብነትም በተለያዩ ርእሶች ላይ ማዕከላዊ መመሪያ መጻሕፍት (Handbook) አዘጋጅቶ ማሰራጨት፣ የፓናል ውይይቶችን ማካሄድ፣ የተለያዩ አስራሮችን በመዘርጋት ችግር ፈቺ እና ተጨባጭ የሆኑ ሥልጠናዎችን መስጠት የሚገኙበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አክለውም የኢ-ለርኒንግ ሥልጠናዎችን በማዘጋጀት ባለሙያው ባለበት ሆኖ እንዲሰለጠን ጥረት እየተደረገ መሆኑን ለአብነትም “በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ወይም ንብረትን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ” በሚል ርዕስ ላይ የተዘጋጀ ሥልጠና በመሰጠት ላይ ያለ መሆኑን አስታውሰው በቀጣይነትም በሴቶችና ሕጻናት ላይ በሚፈፀሙ ወንጀሎች ዙሪያ የኢ-ለርኒንግ ሥልጠና ለመስጠት ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይህ ሥልጠና በክረምት ወራት ፍርድ ቤቶች ሲዘጉ በልዩ ሁኔታ እንዲሰጡ ከተያዙ ስምንት ሥልጠናዎች መካከል አንደኛው መሆኑን ጠቅሰው፤ ተሳታፊዎች በ2016 ዓ.ም በድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተቀጠሩ ዐቃቤያነ ሕግ በመሆናቸው በሥራ ሂደት ውስጥ የሚያስፈልጋቸውን በርካታ ተግባራዊ የሆነ እውቀት እና ችሎታ እንዲያገኙበት ታስቦ መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም የመድረኩ ተሳታፊዎች በሥልጠናው ውስጥ በንቃት መሳተፍ፣ ልምድ መለዋወጥ እንዲሁም ያገኙትን እውቀት በቀጣይነት ተግባር ላይ ማዋል እንደሚጠበቅባቸው አመልክተው ሥልጠናውን በይፋ አስጀምረዋል፡፡

ሥልጠናውም ልምድ ባላቸው የተቋሙ ዐቃቤያነ ሕግ በአቶ አሰፋ ማሬ የልደታ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እና አቶ ጴጥሮስ አራጌ የቂርቆስ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ከነሐሴ 05 እስከ 10 ቀን 2ዐ17 ዓ.ም. በሚቆይ እና በምርመራ፣ በክስ ዝግጅት እንዲሁም የችሎት ክርክር ዙሪያ ትኩረት አድርጎ በሚሰጠው በዚህ ሥልጠና ላይ ከ46 በላይ የሚሆኑ በፍትሕ ሚኒስቴር የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዐቃቤያነ ሕግ እንደሚሳተፉ ተጠቁሟል፡፡

Tagged Under: academic • Advocacy • ali • Capacity Building • case • criminal • Criminal Investigation • Education • handbook • Investigation • launch • learning • lis • preparation • pro • profession • professional • professionalism • ratio • school • special • technical and vocational education and training • technical and vocational education and training (tvet) • Training • trial • trial advocacy • un • winter
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች