ከክልል እና ሁለቱ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮዎች ለተዉጣጡ መካከለኛ አመራሮች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጠ

A capacity-building training was provided for mid-level leaders from the regional and the two city administration justice bureaus

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ህግ፣ትምህርት እና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ስልታዊ መሪነት፤ ስትራቴጂክ ዕቅድ እና የለዉጥ አመራር ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ከክልሎች እና ሁለቱ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮዎች ለተዉጣጡ መካከለኛ አመራሮች ለሁለት ቀናት የቆየ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴር ባደረገዉ የቅድመ ዳሰሳ ጥናት በርዕሰ ጉዳዮቹ ዙሪያ የተለያዩ ክፍተቶች በመለየታቸዉ መሰል የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን በየደረጃው ላሉ የተቋሙ እንዲሁም የክልል አመራሮች መስጠቱ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱ ተገልጿል፡፡

ሥልጠናው በዚህ ደረጃ መስጠቱ የተጠናከረ የፍትሕ ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻል ጠቀሜታዉ የጎላ በመሆኑና አመራሩን ማብቃት ለተቋም ግንባታ ቁልፍ ሚና የሚጫወት በመሆኑ ፍትሕ ሚኒስቴር የሰዉ ሀይል አቅም ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እንደሚገኝ በመድረኩ ተመላክቷል፡፡

Tagged Under: academic administration african charter on the rights and welfare of the child and healthcare administration and control authority building bureau bureaus capacity Capacity Building capacity building training city city administration Education Justice justice bureau leaders learning level medicine and healthcare administration and control authority medicine and healthcare administration and control proclamation no. 661/2009 mid-level oromia regional justice bureau pro ratio rea region Regional Regional Justice Bureaus school Training
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች