ተቋማዊ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ለማሳደግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ስለመሆኑ ተገለፀ

Special Emphasis Being Placed on Enhancing Institutional Technology Adoption

በፍትሕ ሚኒስቴር፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር፣ አቶ ፀጋዬ አማረ፣ ዛሬ በሰጡት ማብራሪያ፣ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ፣ በአዋጅ የተሰጠውን ሥልጣንና ተግባር ለመወጣት በሚያደርገው ሂደት፣ ተቋማዊ አግልግሎቶችን በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ዘዴዎች በማስደገፍ አገልግሎቱን በከፍተኛ ጥራትና ፍጥነት መስጠት ይቻል ዘንድ፣ ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ስለመሆኑ ገልጸዋል፡፡

ዳይሬክተሩ ጉዳዩን በማስመልከት ሲያብራሩ እንደ ሀገር ሥራዎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የማስደገፍና አገልግሎቶችን በጥራት፣ በቅልጥፍና እንዲሁም ተገልጋዮች ካሉበት ቦታ ሆነው ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ አቅጣጫ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን በማስታወሰ ይህንኑ ዉጥን ተግባራዊ ለማድረግም፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች የተቋሙን የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ በውሰዱት ቁርጠኛ አቋም፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሪፎርም ግብረሃ ኃይል ተቋቁሞ ወደ ሥራ ገብቷል ብለዋል፡፡

የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት፣ በሚኒስቴር መ/ቤቱ ያሉ ሁሉም የሥራ ክፍሎች፣ አሰራራቸው በዘመናዊ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን፣ እስከ 2017 ዓ/ም የሚተገበር የረጅም ጊዜ እንዲሁም እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም የሚተገበር ዕቅድ በማዘጋጀት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ዕቅዱ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ሲሆንም የወንጀል ምዝገባ አስተዳደር ሥርዓት (CRMIS) ትግባርን ጨምሮ የወንጀልና የተጠርጣሪ መጠቆሚያ ሥርዓት፣ አገራዊ የወንጀል ዳታቤዝ (crime record)፤የጥብቅና ፍቃድና ማደስ አገልግሎት፤ ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት፤ የሕግ ይረቀቅልኝ፣ ሕግ ይታረምልኝ እንዲሁም መመርያ ይታረምልኝ ጥያቄ፤ የፍትሐብሔራዊ አገልግሎት ጥያቄ፤ የቅሬታና አቤቱታ አቀራረብ እንዲሁም ምላሽ አሰጣጥ ሥርዓት፤ የደብዳቤ ገቢ ወጪ ሥርዓት፤ የይቅርታና ምሕረት መጠየቅያ ስርዓት፤ በፌደራል ተቋማት ያሉትን የፍትሐብሄር ነገረፋጆዎች ሪፖረት መቀበልና ክትትል ማደረግ፣ የተቋሙ ስራዎች የደረሱበትን ደረጃ መከታተያ ዳሽ ቦር ሲስተም፣ ሀገራዊ የፍልሰት እና ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር የወንጀል ፈጻሚዎች ተጠያቂነት ሁኔታ የመረጃ ቋት፤ይቅርታ የተሰጣቸው ታራሚዎች ሀገራዊ የመረጃ ቋት፤ ዓለም አቀፍ የሕግ ትብብር ጥያቄዎች ማስተናገጃ ሲሰተም ማልማትና ሥራ ላይ ማዋል እንዲሁም ሌሎች በርካታ የኢ፟፟-ሰርቪስ አግልግሎቶችን በተሟላ ሁኔታ ለማቅረብ እንደሚያስችል አቶ ፀጋዬ ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓትም የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሪፎርም ሥራዉን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ትራንስፎርሜሽናል ልዩ ዕቅድ ከማዘጋጀት ጀምሮ የተለያዩ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸዉን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

Tagged Under: adoption • criminal • digital • digital transformation • E-Government • information • Information technology • institutional • Institutional Reform • international legal cooperation • Legal Aid • Legal drafting • management • National • record • reform • system • Technology • technology adoption • transformation
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች