የፍትህ ሚኒስቴር የፍትህ ዘርፍ የ2017 በጀት አመት እቅድን አስመልክቶ በከተማ መስተዳደሮች እና ከክልል ፍትህ ቢሮዎች ጋር በጋራ ውይይት አድርጓል

Ministry of Justice Holds Joint Discussion with City Administrations and Regional Justice Bureaus Regarding the Justice Sector's 2017 Budget Year Plan

የፍትሕ ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድን አስመልክቶ የሕግና ፍትሕ ማሻሻያ ስራዎች ፣የፍትሕ አገልግሎት አሰጣጥ ተደራሽነት ፣የወንጀል ስጋትን መቀነስ እና የወንጀል ፍትሕ አገልግሎት ውጤታማነት በሚሉ ይዘቶች በፍትሕ ሚኒስቴር የስትራቴጂክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ደሳለኝ መንግስቴ በኩል ቀርቦ በቀረበው መሪ ዕቅድ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

እንዲሁም በተሳታፊዎች በኩል ግልፅ ያልሆኑ እና ምላሽ የሚፈልጉ ጉዳዮችን አስመልክቶ በተነሱት ጉዳዮች ላይ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስቴር ክቡር ኤርሚስ የማነብርሃን (ዶክተር) እና በአቶ ደሳለኝ በኩል ምላሽና ማብራሪያ ተሰቷል፡፡

በዚህም በተነሱ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ተደርሶበት የተገኙ አመራሮችና ባለሙያዎች የነበረው ውይይትና ማብራሪያ የነበረባቸውን ክፍተቶች የሞላና ለቀጣይ የተሻሉ ስራዎችን ለመሥራት አጋዥ እንደሆነ ተናግረዋል።

Tagged Under: 2017 2017 budget access Access to Justice Budget budget planning Capacity Building city administrations Crime Crime Prevention criminal Criminal Justice desalegn mengiste ermias yemaneberhan Ethiopian Ministry of Justice federal democratic republic of ethiopia (fdre) Justice Justice Sector Reform justice service delivery Legal Reform ministry planning policy dialogue prevention reform Regional Justice Bureaus sector Stakeholder Consultation Strategic Planning
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች