የፍትሕ ሚኒስቴር እና አይኦኤም (IOM) በሶስት አመቱ የፍትህ አካላት የትራንስፎርሜሽን እቅድ ዙሪያ በጋራ ለመስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል

Ministry of Justice and IOM (International Organization for Migration) Discuss Collaboration on Three-Year Justice Sector Transformation Plan

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6/ 2016 ዓ.ም በፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሃን እና የአይኦኤም ኢትዮጵያ ተወካይ ሳራ ባሻ ለሦስት ዓመታት የሚዘልቀውን የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ተባብረው በሚሰሩበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡

ዶ/ር ኤርሚያስ በውይይቱ ወቅት የአይኦኤም ልምድ እና አለም አቀፋዊ ተደራሽነት የትራንስፎርሜሽን እቅዱን ዋና ዋና ጉዳዮችን በመተግበር ረገድ ጠቃሚ ሚና አለው የሚል ጽኑ እምነት እንደዳላቸው የገለጹ ሲሆን ሳራ ባሻ በበኩላቸው አይኦኤም የኢትዮጵያ የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግና የእቅዱን ዓላማ ለማሳካት ከፍትሕ ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

ተቋማቱ ባካሄዱት ምክክር በአቅም ግንባታ ዙርያ፣ በባለሙያ ማጥራት፣ የሕግ ግንዛቤ ለፍትሕ ባለድርሻ አካላትና ማህበረሰቡ በአዲስ እይታ ከመፍጠር አንጻር፣ ሀገር አቀፍ የወንጀል ዳታቤዝ ማደራጀት፣ ሀገራዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስትራቴጂ መቅረፅ እና መተግበር፣ የንቃተ ህሊና የሕግ አገልግሎት ስርዓትን መንደፍና መተግበር፣ የ forensic ምርመራ በክልሎች ተደራሽ ማድረግ፣ የማኅበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ውጤታማነት ማጠናከር እና ሌሎች ላይ ያቶከረ ሀሳቦችን አንስተው ተወያይተዋል።

በመጨረሻም በቴክኒክ ቡድን ደረጃ የበለጠ ለመወያየት በመስማማት ውይይታቸውን አጠናቀዋል።

Tagged Under: Awareness building capacity Capacity Building capacity development Community Policing criminal database forensic science international international organization for migration iom Justice Justice Sector Reform legal Legal Awareness Migration organization plan pro bono legal services reform Rule of Law sector Stakeholder Engagement Technical Assistance three-year plan transformation transformation plan
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች