የፍትህ ሚኒስትሩ ክቡር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ለ2017 በጀት አመት ለተቋሙ አመራሮች የስራ አቅጣጫ ሰጡ

Minister of Justice Honorable Gedion Timothewos (Dr.) Gave Work Direction for the 2017 Budget Year to the Institution's Leaders

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የተቋሙ በ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2017 በጀት ዓመት እቅድ በቀረበበት መድረክ ተገኝተዉ ለአዲሱ በጀት ዓመት ለተቋሙ አመራሮች ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ በሰጡት አቅጣጫም ተቋሙ በ2017 በጀት ዓመት በሁሉም ዘርፎች የተለየ ትኩረት በማድረግ በተለይም የሶስት አመቱን የፍትሕ ዘርፍ የትራንስፎርሜሽን እቅድን ለማሳካት ልዩ ትኩረት በመስጠት ስራዎችን መሥራት እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዉ አሳስበዋል፡፡

በ2016 በጀት ዓመት የታዩ የስራ አፈፃፀሞችን በዘርፍ ከፋፍለዉ ለቀጣይ የስራ አቅጣጫ ያስቀመጡት ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሲጀምሩ ዘርፉ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ በገባበት በዚህ አንድ ዓመት ዉስጥ የስራ ክፍሎቹን አስተባብሮ በመሥራት መልካም ተግባራትን ማከናወኑን ገልጸዉ በተለይም ከክልሎች ጋር ያለን ቅንጅታዊ አሠራር በማሳደግ፣የሶስት ዓመት የፍትሕ ዘርፍ የትራንስፎርሜሽን እቅድ ከሰነድነት አልፎ ስራ ላይ እንዲዉልና መሬት እንዲረግጥ በማድረግ በኩል፣በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስራዎች፣ በማኅበረሰብ አቀፍ የፍትሕ አገልግሎት እና በሌሎች ተግባራት ላይ የታዩ መልካም ዉጤቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

ከመንግሥት ሕግና ፍትሕ ዘርፍ ጋር በተያያዘ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲን በማፀደቅ በኩል ለተቋሙ ጉልህ ሚና እንደነበረዉና ከፌዴራል ህጎች ተፈፃሚነት ጋር በተያያዘም በተለይም የአስተዳደር ስነ-ሥርዓት ህጉን አስመልክቶ የተሰራዉ ስራ መልካም እንደነበር እንዲሁም ከንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ዝግጅት ጋር የተያያዙ ስራዎችን አንስተዉ መሰል የስራ ቁርጠኝነትን አጠናክሮ በማስቀጠል በሌሎች በዘርፉ ስር ያሉ የስራ ክፍሎች ዉስጥ በተለይም የፍትሐብሄር የስራ ክፍልን በሰዉ ኃይል፣ በሥልጠናና በአቅም ግንባታ እያጠነከሩ መሄድ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ጋር በተያያዘ በ2017 በጀት ዓመት ልዩ ትኩረት እንደሚያስፈልግ የተናገሩት ክቡር ሚኒስትሩ በቅርቡ በዘርፉ ስር ባሉ የስራ ክፍሎች የተደረገዉን የአመራር ለዉጥ ተከትሎ በ2017 ዓ.ም ሙሉና አዲስ በጀት ዓመት በመሆኑ ከአሠራር፣ ከአመለካከትና ከአደረጃጀት አኳያ አዲስ እይታን በማምጣት መሥራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ የአስተዳደር ዘርፉ በተለይም ባለፉት አመታት ከነበሩት አሰራሮች ወጣ ብሎ የተሻለና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት በኩል መልካም ተግባራትን ማከናወኑን ገልፀዉ ይህንኑ ተግባር አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ እና ለዚህም ለዘርፉ አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በጥቅሉ የ2016 በጀት ዓመት ተቋሙ ከዉስጥም ሆነ ከዉጭ የነበሩበትን ተግዳሮቶች ተቋቁሞ በአመራርም ሆነ በፈፃሚዉ በኩል መልካም እንቅስቃሴዎች የታዩበትና በዚህም ጥሩ አፈፃፀሞች የተመዘገበቡት ዓመት መሆኑን የገለጹት ክቡር ሚኒስትሩ በ2017 በጀት ዓመት ቀደም ብሎ የተጀመሩ ስራዎችን ሙሉ ለሙሉ ማጠናቅቅ ላይ በማተኮር የተሻለ የስራ አፈፃፀም የምናስመዘግብበት ዓመት እንዲሆን በሙሉ አቅማችን መረባረብ እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ የፍትሕ ሚኒስትሩን ክቡር ጌዲዮን ጢሞቲዎስን (ዶ/ር) ጨምሮ፣ሚኒስትር ዲኤታዎች፣ የተቋሙ መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም ቡድን መሪዎች ተገኝተዋል።

Tagged Under: budget year 2017 Government Planning Legal Reform Performance Report
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች