ወንጀልን ለመከላከል በቅድሚያ አስፈፃሚ ተቋማት በወንጀል መከላከል ስትራቴጂ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ ሊኖራቸው እንደሚገባ ተጠቆመ

It is Indicated that Executive Institutions Should First Have Sufficient Understanding of the Crime Prevention Strategy to Prevent Crime

የፍትሕ ሚኒስቴር ከዩ.ኤን.ኦ.ዲሲ ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አገር አቀፍ የተቀናጀ የወንጀል መከላከል ስትራቴጂ እና የማስፈፀሚያ ስልቶች ላይ ለፍትሕ አካላትና ከተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ሥልጠና ሰጥቷል።

ትንንሽ ከሚባሉ ወንጀሎች ጀምሮ እጅግ ውስብስብ ወንጀሎች በህብሰተሰቡና በአገር ሰላምና እድገት ላይ ከባድ ችግር እያደረሱ እንደሚገኙና እነዚህን ወንጀሎች ለመከላከልም ፓሊሲ፣ስትራቴጂ፣ዝርዝር ህጎች እንዲሁም የተቋማት አደረጃጀትና ጠንካራ አሰራሮች አስፈላጊ መሆናቸውን በፍትሕ ሚኒስቴር የመንግሥት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አማካሪ አቶ ሳምሶን ተገኔ ገልፀዋል።

በዚሁ መሠረትም የችግሩን ጥልቀትና ስፋት ከግምት ውስጥ ያስገባ አገር አቀፍ የወንጀል መከላከል ስትራቴጂ መዘጋጀቱንና እነዚህን ህጎች ለሚያስፈፅሙ አካላት የአቅም መገንቢያ ሥልጠና መስጠት አስፈላጊ ነው ሲሉ ፍትሕ ሚኒስቴርም ሀላፊነቱን ለመወጣት ሥልጠናውን አዘጋጅቷል ብለዋል።

ቀጥሎም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አገር አቀፍ የተቀናጀ የወንጀል መከላከል ስትራቴጂን ያቀረቡት በተቋሙ የዐቃቢያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ ፅ/ቤት ሃላፊ እና የስትራቴጂው አርቃቂ ቡድን አስተባባሪ አቶ ጌታነህ ሀብታሙ በገለፃቸው የስትራቴጂው ምንነት፣ዓላማ፣አስፈላጊነት፣መነሻ ሁኔታ፣ጠቅላላ የወንጀል መከላከል ደረጃና ሞዴል፣ስትራቴጂው ትኩረት የሰጣቸው 10 የወንጀል ድርጊቶች እና መከላከያ መንገዶች ተዳስዋል።

የወንጀል መከላከል ዋና ዓላማም የሕዝብና የባለድርሻ አካላትን ንቁ ተሳትፎ ባረጋገጠ መንገድ በአገሪቱና በህዝቦች ሰላም ደኅንነትና ጥቅሞች ላይ የሚፈፀሙ ፤ለህብረተሰቡ ዋና ስጋት የሆኑ ወንጀሎችን በመከላከል መቀነስና፤ የዜጎችን ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች በማስከበር የአገሪቱን ሰላምና ደኅንነት ማስጠበቅ መሆኑ ተገልፆል።

የወነጀል መከላከል ስትራቴጂው በልምድ ሲሰሩባቸው የቆዩና ወንጀለኞችን በማሳደድ ለሚጠፋው ጊዜና ወጭ መለስ ብሎ ወንጀሉን ቀድሞ ለመከላከልና ከምንጩ ለመቆጣጠር የሚያነሳሳ መሆኑን የገለፁት የሥልጠናው ተሳታፊዎች በተዋረድ ህብረተሰቡን በማስተማርና ግንዛቤ በመፍጠር መከላከሉ ላይ አጋዥ አድርጎ መሥራት ያስፈልጋልም ብለዋል።

Tagged Under: building • capacity • Capacity Building • civil liberties • Crime • Crime Prevention • crime prevention strategy • criminal • Criminal Code • Criminal Justice System • Education • fundamental rights • Human Rights • integrated crime prevention • Justice • Law Enforcement • learning • National Strategy • Police • Policy • prevention • public safety • Rule of Law • Security • skill development • stakeholders • Strategy • system • Training • UNODC
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች