የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

Ethiopia's Ministry of Justice and Addis Ababa Police Commission Sign Cooperation Framework Agreement

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ፍትሕ ስርዓቱን ለማሻሻል የሚያስችል በወንጀል ምርመራ፣ ክስ እና ክርክር ሂደት ላይ በጋራ የሚተገበሩ ጉዳዮችን በተሻለ ቅንጅት እና ውጤታማነት ለመፈጸም የሚያስችላቸውን የትብብር ስምምነት ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ተፈራርመዋል፡፡

በትብብር ማዕቀፍ ስምምነት የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሐና አርዓያሥላሴ በሁለቱ ተቋማት መካከል የሚደረገው የጋራ ስምምነት በወንጀል ምርመራ እና ክስ ሂደት ላይ የሚኖረውን የተልዕኮ አፈጻጸም ከማቀላጠፍ ባለፈ የወንጀል ፍትሕ ስርዓቱ ላይ መሠረታዊ የሥራ ባህል ለውጥ ማምጣት የሚያስችል መሆኑን ገልጸው፤ በቀጣዩ ዓመት በወንጀል ፍትሕ ስርዓቱ ላይ የተሻለ ውጤትን ለማምጣት ከወዲሁ በቅንጅት የመሥራት ሂደቱን በመጀመር የስራ አፈፃፀሙንም እየገመገሙ መሄድ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ጌቱ አርጋው በበኩላቸው ሁለቱ ተቋማት ለአንድ ዓላማ የሚተጉ ተቋማት በመሆናቸው እንዲሁም ህብረተሰቡ ለሚያነሳቸው የፍትሕ ጥያቄዎች በተናጠል ምላሽ መስጠት ስለማይቻል ተቀናጅቶ በጋራ መስራቱ አገልግሎቱን የተሟላ የሚያደርገው መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህ ስምምነት ከዚህ ቀደም በተለያዩ ምክንያቶች ከአንዱ ወደ ሌላኛው አካል እየተመላለሱ የቆዩ የወንጀል መዛግብትን አፋጣኝ መፍትሔ እንዲያገኙ የሚያስችል እንዲሁም በቀጣይ የሚኖረውን አጠቃላይ የወንጀል ፍትሕ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሳለጥ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች