በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የስትራቴጂ ዕቅድ ዝግጅት ላይ ያተኮረ የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት ተካሄደ

Input Collection Discussion Held on the Strategic Plan Preparation of the Ministry of Justice of FDRE

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ለተቋሙ የ5 ዓመት ስትራቴጂ እቅድ ዝግጅት ግብዓት ለማሰባሰብ የሚያስችል ውይይት አካሂደዋል፡፡

ባለፉት 5 አመታት ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው የስትራቴጂ እቅድ የጊዜ ገደብ በመጠናቀቁ፤ ለቀጣዩ ጊዜ አዲስ ራዕይ እንዲሁም ግብ ማስቀመጥ ተገቢ በመሆኑ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት ካሉ ሀገራዊ እና አለምአቀፍ ሁኔታዎች ከሚገኙበት ነባራዊ ሁኔታ ጋር አብሮ መጓዝ የሚያስችልና ራስን ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተመጣጣኝ አድርጎ የሚያስቀጥል አዲስ የ5 ዓመት ስትራቴጂ ዕቅድ ማዘጋጀት በማስፈለጉ የውይይት መድረኩ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ወ/ሮ ሐና አርዓያስላሴ እንዳሉት በቀጣይ የሚዘጋጀው የ5 ዓመት የስትራቴጂ ዕቅድ ዝግጅት መነሻ የሚሆኑ አበይት ጉዳዮችን አስመልክቶ ተቋሙ ባለፉት አምስት አመታት የነበረውን የዕቅድ አፈፃፀም ሁኔታ፣ የውስጥና የውጪ ባለድርሻ አካላት እና የተገልጋዮች አሰተያየትን መሠረት በማድረግ በተጨማሪም ባለፉት 10 አመታት ውስጥ እንደ ተቋም የተቀመጠው ራዕይ እና ግብ ላይ የሁሉንም የስራ ሃላፊ እና ሠራተኛ ያለውን መረዳት ለመፈተሽ የሚያስችሉ የዳሰሳ ጥናቶች መደረጋቸውን ገልፀዋ፡፡

ለቀጣዮቹ 5 አመታት እንዲያገለግል ለሚዘጋጀው የፍትሕ ሚኒስቴር የስትራቴጂ ዕቅድ ሰነድ መነሻ የሆኑ ነጥቦችን አስመልክቶ፤ ጠቃሚ የሆኑ የሕግ ማዕቀፎችና የፖሊሲ ሰነዶች፣ በተለያየ ወቅት የተሰሩ የጥናት ውጤቶች፣ በባለድርሻ አካላት ትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች፣ የተቋሙ ተገልጋዮች አስተያየቶች፣ የተቋሙ ሰራተኞች የሰጧቸው ግብረመልሶች እንዲሁም ባለፉት አምስት አመታት ቁልፍ የነበሩ አፈፃፀሞች በጥልቀት ታይተው ለሰነዱ መነሻ ተደርገው መወሰዳቸውን የተገለጸ ሲሆን፤ በአጠቃላይ በየዘርፉ የተመዘገቡ ውጤቶች እና ደካማ ናቸው የተባሉ ጉዳዮች ተካተው ሰፋ ያለ ገለፃ ተደርጓል፡፡

በመጨረሻም የቀረበውን የመነሻ ሰነድ ተከትሎ በተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፤ እንደ ተቋም ያሉ ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት አስተካክሎ መሄድ፤ በሌላም በኩል በቀጣይነት ያሉ ስራዎችን ለማከናወን ቀደም ሲል ከነበረው አፈፃፀም የነበሩትን ስኬቶች እና ጥንካሬዎችን በመለየት እነዚህን ስኬቶች አጉልቶ መጓዝ እንዲሚያስፈልግ በበላይ አመራሩ አቅጣጫ ተስጥቶ መድረኩ ተጠናቋል፡፡

Tagged Under: assessment • Consultation • Documents • evaluation • feedback mechanism • five-year • five-year plan • frameworks • goals • Input Collection • legal • Legal Frameworks • needs • needs assessment • objectives • performance • Performance Evaluation • performance indicators • plan • plan implementation • planning • Policy • policy documents • stakeholder • Stakeholder Consultation • strategic • Strategic Planning • vision
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች