የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ታሪካዊና አስተማሪ ስራ አከናወነ

Historic and Educational Proceedings Conducted by the Federal High Court Lideta Branch

በዐቃቤ ሕግ የክስ ዝርዝር ላይ ተሹ ካሱ ኢርኮ የተባለው ተከሳሽ ሰውን ለመግደል በማሰብ መጋቢት 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 7፡30 ሰዓት ሲሆን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ሰሚት እንዶዴ አካባቢ የቀድሞ የትዳር አጋሩ እና የአራት ልጆች እናት የሆነችውን የግል ተበዳይ አዳነች ለገሰን በስታር ሽጉጥ ሁለት ጊዜ ተኩሶ አንዱ ስቷት የግንብ ብሎኬት የመታ እና ብሎኬት ውስጥ የጥይት እርሳሱ የተገኘ ሲሆን መጀመሪያ የተኮሰው አንድ ጥይት የግል ተበዳይ የጀርባ አከርካሪ አጥንቷን መቷት ስትወድቅ የፊት የታችኛው ሁለት ጥርሷ እንዲወልቅ፣ የላይኛው መካከለኛ የግራ በኩል ጥርሷ እንዲነቃነቅ፣ የጎድን አጥንቷ እንዲሰበር፣ አከርካሪ አጥንቷ ላይ ያረፈው ጥይት ሰውነትዋ ውስጥ በመቀርቀሩ ምክንያት የቀኝ ሳንባ አየር ዝውውር እንዲቀንስ፣ በወገቧ እና ከወገቧ በታች በቋሚነት ሽባ እንድትሆን፣ ሽንቷ እና አይነምድሯ እንዳትቆጣጠር፣ የመተንፈስ አቅም በቋሚነት መቀነስ እና የአልጋ ቁራኛ በመሆኗ ምክንያት ጀርባዋና መቀመጫዋ አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የስጋ መቦርቦር እንዲደርስባትና በህይወት የመቆየት እድሏ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ በማድረጉ በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ በሴቶችና ህጻናት ላይ ሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት በግድያ ሙከራ ወንጀል በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት ክስ አቅርቦበታል፡፡

ተከሳሽም ክሱን ክዶ የተከራከረ በመሆኑ ዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን አቅርቦ ማሰማቱን የቀጠለ ሲሆን በቀን 13/05/2017 ዓ.ም የግል ተበዳይ በደረሰባት ከፍተኛ ጉዳት ምክንያት በዊልቸርም ሆነ በስትሬቸር መንቀሳቀስ እንደማትችልና በየ1፡00 ሰዓቱ ሰውነቷ እያገላበጡ ማጽዳት እንደሚያስፈልግ በሕክምና በመረጋገጡ ምክንያት ዐቃቤ ሕግ የግል ተበዳይ ከተኛችበት ቤትዋ ሆና የምስክርነት ቃሏን እንድትሰጥ ችሎቱን በመጠየቅና ችሎቱም ይህንኑ በመፍቀድና በማመቻቸት የግል ተበዳይ ከቤቷ ሆና በፕላዝማ የምስክርነት ቃሏን እንድትሰጥ የተደረገ ሲሆን ይህንንም ተበዳዩዋ በደረሰባት ከፍተኛ አካላዊ ጉዳት ምክንያት በአካል ፍ/ቤት ቀርባ የምስክርነት ቃል ለመስጠት ባለመቻሏ የሚጓደልባትን ፍትሕ በእጅጉ የሚቀንስና ለሌሎችም አስተማሪ የሆነ ተግባር ሆኖ ተገኝቷል፡፡

Tagged Under: Attempted Murder Criminal Case Federal High Court
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች