በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተሕግ፣ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለድሬዳዋ መርማሪ ፖሊሶች የወንጀል ምርመራ መሰረቶች ፣የወንጀል ምርመራ ዓይነቶች ፣የማስረጃ ሕግና ምርመራ መሰረቶች እና የምርመራ ስነልቦና በሚሉ ይዘቶች ላይ በማተኮር ከታህሳስ 21 እስከ ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ስልጠና ተሰቱዋል፡፡
በስልጠና መድረኩ የንቃተ ሕግ ፣ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ከተቋሙ ተግባርና ኃላፊነት አንፃር የውስጥና የውጭ የመንግስት ባለሙያዎችን በሕግና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠናና የንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና በመስጠት ባለሙያዎች ስነ-ምግባርን ጠብቀው ግዴታቸውን እንዲወጡ ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎችን እና የምክክር መድረኮችን እንደስልጠናዎች ርዕሰ ጉዳይ የሚዘጋጅ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
የስልጠናው አላማ ሰልጣኞች በስራ ሂደታቸው እየገጠማቸው ያለውን ጉዳይ አንስተው በሚገባ ውይይት በማድረግ ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ ማስቻል ሲሆን፤ በነበራቸው በሁለት ቀን ቆይታም ስልጣኞች የዕርስ በርስ ልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበትን አስቻይ ሁኔታ መፍጠር መቻሉ የተገለጿል፡፡
ተመሳሳይ ስልጠናዎች ለፌዴራል እና አዲስ አበባ ፖሊስ የምርመራ አባላት መሰጠቱ በመድረኩ ተመላክቷል፡፡