የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር ከጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎሽፕ ኢትዮጵያ ጋር በሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ትግበራ ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

FDRE Ministry of Justice and Justice for All Prison Fellowship Ethiopia Agree to Collaborate on the Implementation of the Transitional Justice Policy

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ከጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎሽፕ ኢትዮጵያ ጋር በሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ትግበራ ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

በመግባቢያ ፊርማ ስነስርዓት ላይ የፍትሕ ሚኒስቴርን ወክለው የፈረሙት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የመንግሥት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ ሲሆኑ የጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎሽፕ ኢትዮጵያን በመወከል ደግሞ የፈረሙት የተቋሙ ፕሬዚዳንት ፓስተር ዳንኤል ገብረስላሴ ናቸው፡፡

የጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎሽፕ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ከፍትሕ ሚኒስቴር ጋር በተለያዩ ጉዳዮች በጋራ ሲሰራ እንደነበር ያወሱት ሚኒስትር ዴኤታው በአሁን ሰዓት የሽግግር ፍትሕ ማስተግበሪያን መንግሥት ለብቻው መሥራት እንደማይችል ይልቁንም የተለያዩ ባለድራሻ አካላት ተሳትፎን የሚጠይቅ መሆኑን ገልፀው በዛሬው ዕለት ከጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎሽፕ ኢትዮጵያ ጋር ያደረግነው ስምምነት የዚሁ አንድ ክፍል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ፓስተር ዳንኤል በበኩላቸው ተቋማቸው ከፍትሕ ሚኒስቴር ጋር በመሆን የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን አንስተው በቀጣይም በሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ትግበራ ዙሪያ ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶችን በማስተባበር የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የልምድ ልውውወጥ ስራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም የሁለቱ ተቋማት ተወካዩች በተዘጋጀው የመግባቢያ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩ ሲሆን ስምምነቱም ለቀጣይ ሶስት ዓመታት የሚቆይ ሆኖ እንዳስፈላጊነቱ የሚራዘም መሆኑ ተመላክቷል፡፡

Tagged Under: agreement Capacity Building civil civil liberties Civil Society Organizations Collaboration collaboration agreement Conflict Resolution fellowship fundamental rights Human Rights Implementation international international organizations Justice justice for all prison fellowship ethiopia Legal Reform memorandum Memorandum of Understanding organizations Policy Policy Implementation prison society Stakeholder Engagement transitional transitional justice understanding
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች