ተጎጂ ፍልሰተኞችና ተጋላጭ የማኅበረሰብ ክፍሎች የሚፈልጉትን አገልግሎት ካሉበት ቦታ ሆነው የፈለጉትን መረጃና አገልግሎት ማግኘት የሚያስችላቸው የዲጂታል አገልግሎት ጠቋሚ ዛሬ በስራ ላይ ውሏል፡፡
የዲጂታል አገልግሎት ጠቋሚ መክፈቻ መርሐግብርን አስመልክቶ በተካሄደው መድረክ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ተወካይ Michele Shivo እንዳሉት ለተጎጂ ፍልሰተኞችና ለተጋላጭ የማኅበረሰብ ክፍሎች የዲጂታል አገልግሎት ጠቋሚ በዛሬው ዕለት በይፋ መከፈቱ ለተጎጂ ፍልሰተኞችና ለተጋላጭ የማኅበረሰብ ክፍሎች ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በመቀጠል ንግግር ያደረጉት በፍትሕ ሚኒስቴር የብሔራዊ ትብብር ጥምረት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብረሃም አያሌው የብሔራዊ ትብብር ጥምረቱ ከGIZ የተሻለ የፍልሰት አስተዳደር ፕሮግራምጋር በመተባባር ከዚህ በፊት የሚሰጠውን አገልግሎት በመፅሀፍ መልክ አሳትሞ ማሰራጨቱን ተናግረዋል፡፡
እ.ኤ.አ ከ2021 ጀምሮ ዲጂታል ወረቀት ላይ ይጠፋል ፣አመራሮች (ግለሰቦች) ሊቀየሩ ይችላሉ እና ተቋማት አድራሻቸውን ወይም የሚሰጡትን አገልግሎት ሊቀይሩ ይችላሉ የሚለውን ታሳቢ በማድረግ የኦንላይን ፕላትፎርም ዲጂታል ሆኖ ተጎጂ ፍልሰተኞችና ተጋላጭ የማኅበረሰብ ክፍሎች በሞባይልና በኮምፒዩተር አማካኝነት ያለምንም ውጣ ውረድና ልፋት የሚፈልጉትን አገልግሎትና መረጃ ካሉበት ቦታ ሆነው በቀላሉ ማግኘት የሚያስችላቸው እንዲሆን ተደርጎ በዛሬው ዕለት አገልግሎት በይፋ ስራ መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡
የዲጂታል አገልግሎት ጠቋሚው ፕላት ፎርም ተጎጂ ፍልሰተኞችና ተጋላጭ የማኅበረሰብ ክፍሎች ነፃ የሕግ ድጋፍ ፣የጤና፣ የመጠለያ ፣ የትራንስፖርት ፣የመልሶ ማቋቋም እና የነፍስ አድን አገልግሎት የሚሰጡ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የት እንደሚገኙ? ምን አይነት አገልግሎት እንደሚሰጡ የሚያስችል ዝርዝር መረጃ የያዘ መሆኑን አውሰተዋል፡፡
የዲጂታል አገልግሎት መስጫ ተጎጂ ፍልሰተኞችና ተጋላጭ የማኅበረሰብ ክፍሎች አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት ቀልጣፋ፣ቀላል በአንድ ጊዜ ለሁሉም አካላት በቀላሉ መዳረስ የሚችል ከመሆኑ ባለፈ አገልግሎቱን የሚሰጡ ተቋማት ያላቸውን የስራ ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክር መሆኑን የተናገሩት አቶ አብርሃም ብሔራዊ የቅብብሎሽ ስርዓቱ የተሻለ እንዲሆን ለማድረግ ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
አቶ አብረሃም በንግግራቸው ፅህፈት ቤቱ የወንጀል መረጃ ቋትን እያለማ እንደሚገኝ እንዲሁም በትብብር ጥምረት ማዕቀፍ ውስጥ በኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት አማካኝነት ብሔራዊ የሆነ ዳታ ቤዝ እየለማ እንዳለና በሴቶችን ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካኝነት የተመላሾች ዳታ ቤዝ እየለማ መሆኑን ገልፀው ወደፊት ከነዚህ ዳታ ቤዞች ጋር የማስተሳሰር ስራ እንደሚሰራ አመላክተዋል፡፡
አገልግሎት መስጫው የሚመራው በፍትሕ ሚኒስቴር የብሔራዊ ትብብር ጥምረት ፅህፈት ቤት መሆኑ የገለፁት ኃላፊው ይንንን ድጋፍ ያደረጉት GIZ ከተሻለ የፍልሰት አስተዳደር ፕሮግራም ጋር በመተባባር መሆኑን አውስተዋል፡፡
በዛሬው ዕለት በይፋ የዲጂታል አገልግሎት ፕላት ፎርምን ከሀገራችን ባሻገር ኬኒያ፣ኡጋንዳና ሶማሌ ላንድ አዲስ አበባ በመገኘት ክፍለ አህጉራዊ አገልግሎቱን በይፋ አስጀምረዋል፡፡