ምቹ የሥራ ከባቢ ለላቀ የፍትሕ አገልግሎት አሰጣጥ

Conducive Work Environment for Optimal Justice Service Delivery

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ህንፃ እንዲሁም የተቋሙ ድህረ-ገፅ በዛሬው ዕለት የተቋሙን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት መስከረም 8/2018 ዓ.ም በይፋ ተመርቋል፡፡

በምረቃ መርሃ-ግብሩ መንግሥት በፍትሕ ተቋማት የሚሰጡ አገልግልቶች ውጤታማ፣ ቀልጣፋ፣ ተደራሽ እና ምቹ እንዲሆኑ በየተቋማቱ የፍትሕ ትራንሰፎርሜሽን ዕቅድ ተዘጋጅቶ እንዲተገበር በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ዘርፍ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

ፍትሕ ሚኒስቴር በሶስት ዓመቱ የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከያዛቸው የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ተግባራት መካከል አንዱ የሥራ ቦታን ለተገልጋዮች እና አገልግልት ለሚሰጡ ባለሙያዎች ምቹ እና ተደራሽ በማድረግ ቀልጣፋ እና ጥራት ያለው አገልግልት መስጠት መሆኑ በመድረኩ ተወስቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ተቋሙ በያዘው ዕቅድ መሰረት በቅርቡ በአዲስ አበባ፤ በኮልፌ እና በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተሞች የዐቃቤ ሕግ እና የፍርድ ቤት አገልግሎት የሚሰጡ አዲስ ሕንጻዎችን በማሰራት ለአገልግልት ክፍት ማድረጉ እንዲሁም በሐዋሳ እና ድሬደዋ ከተሞች የሚገኙ አገልግልት የሚሰጡ የተቋሙን ነባር ሕንፃዎችን በማደስ ለአገልግሎት ምቹ የማድረግ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

በተያያዘ እንዲሁ ተቋሙ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ከማስተዋወቅ ባለፈ ለተጣቃሚዎች እንደ አስፈላጊነቱ በቀላሉ የተሟላ መረጃን መስጠት የሚችል ተቋማዊ ድህረ-ገፅ ለምቶ በይፋ ተበስሯል፡፡

በመርሃ-ግብሩ ለህንፃው ዕድሳትና ግንባታ እንዲሁም ለድረ-ገፁ መልማት አስተዋፅኦ ላበረከቱ ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦች ዕውቅና ተሰጥቷል፡፡

Tagged Under: Access to Justice accreditation service fee addis ababa justice bureau administrative justice agency for civil society organizations aid delivery air service agreement arab bank for economic development in africa arra (agency for refugees and returnees affairs) decentralized service delivery delivery environment health service delivery integrated service delivery Justice justice for all Justice For All - PF Ethiopia justice for all prison fellowship ethiopia justice service delivery live Public Service Delivery Service Service Delivery service delivery improvement service delivery standards vice work work environment
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች