የወንጀል ምርመራን የሚመሩ አካላት የተጠርጣሪዎችን እና በቁጥጥር ስር ያሉ ሰዎች አያያዝ እና የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃን ለማረጋገጥ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ተመላከተ

Authorities leading criminal investigations have been urged to play a proactive role in upholding the rights of suspects and detainees

የኢ.ፌ.ድ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የሰብዓዊ መብቶች ዳይሬክቶሬት ከ DANISH INSTITUTE FOR HUMAN RIGHTS ጋር በመተባበር በወንጀል ምርመራ ወቅት የተጠርጣሪዎች እና በቁጥጥር ስር ያሉ ሰዎች አያያዝና የስብዓዊ የመብቶች ጥበቃ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ወርክሾፕ ከፌደራል፤ አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን፤ ከፍትሕ ሚኒስቴር ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እንዲሁም ከአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ አመራሮች ጋር ለሁለት ተከታታይ ቀናት ተካሂዷል፡፡

ወርክሾፑ በዋናነት ዓላማ ያደረገው በወንጀል ምርመራ ሂደት ተሳታፊ የሆኑ የፍትሕ አካላት ተጠርጣሪዎች እና በቁጥጥር ስር ያሉ ሰዎች አያያዝ እና የስብዓዊ መብቶች ጥበቃን በተመለከተ በሕግ የተጣለባቸውን ሃላፊነቶች ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመወጣት የሚያግዛቸውን መድረክ በማመቻቸት የጋራ የሆነ ዝርዝር የድርጊት- መርሃግብር እንዲያዘጋጁ አስቻይ ሁኔታን መፍጠር መሆኑ ታውቋል፡፡

በመድረኩ የተጠርጣሪዎች እና በቁጥጥር ስር ያሉ ሰዎች መብቶች ዓለም አቀፍ እና የሃገር ውስጥ የህግ ማዕቀፎችን፤ የተጠርጣሪዎች የጉብኝት ማኑዋል እና በፍትሕ ሚኒስቴር በ2017 እና 2018 በጀት ዓመት የተካሄዱ የተጠርጣሪዎች ጉብኝት ሪፖርት ፤ የስብዓዊ መብቶች ክትትልን በተመለከተ የፍትሕ ሚኒስቴር ሃላፊነት፤ የፓሊስ ማኑዋል፤ በፍትሕ ሚኒስቴር እና በፌደራል እንዲሁም በአዲስ አበባ ፖሊስ መካከል የተደረጉ የመግባቢያ ስምምነቶች ይዘትን በተመለከተ ለውይይት መነሻ የሚሆኑ ሰነዶች እንዲሁም የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን የዘርፉ ተሞክሮ ቀርቧል፡፡

ተሳታፊዎቹ የቀረቡ የውይይት ሰነዶችን መነሻ በማድረግ በየተቋማቸው በዘርፉ ከዚህ ቀደም የነበሩበትን እንዲሁም አሁን ያሉበትን ደረጃ በመዳሰስ ያላቸውን መልካም ተሞክሮዎችን እና ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች ያጋሩ ሲሆን፤ በዚህም ረገድ የጋራ ድርጊት መርሃግብር ማዘጋጀቱ በጋራ የተሰጣቸውን ሃላፊነቶች መሰረት በማድረግ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም ተሳታፊዎች በምርመራ ወቅት እና በማቆያ ቦታ የተጠርጣሪዎችን መብቶች አጠባበቅን ለማሻሻል እና በዚሁ ሂደት ላይ በፖሊስ እና ዐ/ሕግ መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር የሚያስችል ተግባራዊ የድርጊት መርሃ-ግብር እንዲሁም የክትትል ማዕቀፍ መፍጠር በሚቻልባቸው ጉዳዩች ላይ ሰፋ ያለ የቡድን ውይይት በማድረግ የጋራ የድርጊት መርሃግብር አዘጋጅተዋል፡፡

Tagged Under: act african charter on the rights and welfare of the child authorities criminal Criminal Investigation Criminal Investigations danish institute for human rights decree holding human Human Rights illegal act institute Investigation Investigations itu law legislation old Policy pro proclamation Regulation right Rights statute Suspect
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች