የወንጀል ምርመራ፣ የክስ ዝግጅትና የችሎት ክርክር ማስገንዘቢያ ረቂቅ መፅሐፍ ላይ የግብአት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሔደ

An Input Collection Forum Was Held on the Draft Handbook for Criminal Investigation, Charge Preparation, and Court Litigation

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ-ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳሬክቶሬት አማካኝነት የተዘጋጀ የወንጀል ምርመራ ከስ እና የችሎት ክርክር ማስገንዘቢያ የመፅሐፍ ረቂቅ ላይ የግብአት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሂዷል፡፡

በፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ፤ ትምህርትና ሥልጠና ዳሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ እንዳላካቸው ወርቁ በመድረኩ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም በየአመቱ በተለያየ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ትኩረት ያደረጉ ማስገንዘቢያ መፅሐፍት ታትመው እንዲሰራጩ የሚደረግበት ሁኔታ እንዳለና በዚህም መሠረት በሙስና ወንጀሎች፣ በኢኮኖሚ፤ በሴቶችና ሕፃናት ላይ በሚፈፀሙ ወንጀሎች ዙሪያ ማስገንዘቢያ መፅሐፍት (ሀንድቡክ ) ተዘጋጅተው መሰራጨታቸውን አውስተዋል፡፡ በ2017 በጀት ዓመትም እንዲሁ በወንጀል ምርመራ ክስ ዝግጅት እና የችሎት ክርክር ላይ ያተኮረ ማስገንዘቢያ መፅሐፍ ረቂቅ ተዘጋጅቶ በሁሉም የስራ ክፍሎች አስተያየት እንዲሰጥበት መደረጉን ገልፀዋል፡፡

አክለውም ይህ በወንጀል ምርመራ፤ ክስ ዝግጅት እና የችሎት ክርክር ላይ ያተኮረ ማስገንዘቢያ መፅሐፍ እንዲታተም ማድረግ ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያቶች ውስጥ አንዱ በስራው ለቆዩ እንዲሁም አዲስ ለሚመጡ ዐቃብያነ ሕግ እንደ ማጣቀሻ ሆኖ እንዲያገለግል ማድረግ መቻል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በወንጀል ምርመራ ክስ እና የችሎት ክርክር ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ማስገንዘቢያ እንዲዘጋጅ መደረጉ የሕግ አስፈፃሚ አካላትን አቅም ለመገንባት የሚያግዝ ከመሆኑ በተጨማሪ በስራው ላይ ቀደም ሲል ሲያጋጥሙ የነበሩ ክፍተቶችን በመሙላት ወጥ የሆነ የወንጀል ፍትሕ ስርዓት እንዲኖር ማድረግ የሚያስችል መሆኑን ዳይሬክተሩ አመላክተዋል፡፡

በማስገንዘቢያ መልክ የሚዘጋጁ መፅሐፍትና ሰነዶች የጋራ መገልገያ በመሆን እንደ ማጣቀሻ የሚያገለግሉ በመሆናቸው ጠቀሜታቸው የጎላ እንደሆነ የተጠቆመ ሲሆን፣ የወንጀል ምርመራ ስራ እንዲሁም አጠቃላይ ክስ እና ክርክርን በሚመለከት በዐቃብያነ ሕግ የሚከናወኑ አበይት ተግባራት ተለይተው የተቀመጡበት እንደሆነ ተገልፆል፡፡

Tagged Under: Amhara Regional State • Capacity Building • charge • corruption crimes • court • Court Litigation • criminal • Criminal Investigation • Criminal Justice System • Economic Crimes • handbook • handbooks • Investigation • Justice • legal • Legal Frameworks • Legal Training • Litigation • materials • preparation • Prosecutor • Prosecutor training • system • Training • training manual
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች